New Amharic Standard Version

ምሳሌ 4:1-27

ጥበብ ከሁሉ በላይ መሆኗ

1ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤

ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ።

2በጎ ትምህርት እሰጣችኋለሁ፤

ስለዚህ ትምህርቴን አትተዉ።

3በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣

ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣

4አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤

“ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤

ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ።

5ጥበብን አግኛት፤ ማስተዋልን ያዛት፤

ቃሌን አትርሳ፤ ከእርሷም ዘወር አትበል።

6ጥበብን አትተዋት፤ እርሷም ከለላ ትሆንሃለች፤

አፍቅራት፤ እርሷም ትጠብቅሃለች።

7ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤

ያለህን ሁሉ4፥7 ወይም ያገኘኸውን ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት።

8ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤

ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤

9በራስህ ላይ ሞገሳማ አክሊል ትደፋልሃለች፤

የክብር ዘውድም ታበረክትልሃለች።

10ልጄ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ ቃሌንም ልብ በል፤

የሕይወት ዘመንህም ትበዛለች።

11በጥበብ ጐዳና አስተምርሃለሁ፤

ቀጥተኛውንም መንገድ አሳይሃለሁ።

12ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤

ስትሮጥም አትደናቀፍም።

13ምክርን አጥብቀህ ያዛት፤ አትልቀቃት፤

ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።

14ወደ ኀጥኣን ጐዳና እግርህን አታንሣ፤

በክፉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፤

15ከዚያ አትድረስ፤ አትጓዝበት፤

ሽሸው፤ መንገድህን ይዘህ ሂድ፤

16ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤

ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ ባይናቸው አይዞርም።

17የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤

የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

18የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣

ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።

19የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤

ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም።

20ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤

ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ።

21ከእይታህ አታርቀው፤

በልብህም ጠብቀው፤

22ለሚያገኘው ሕይወት፤

ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና።

23ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤

የሕይወት ምንጭ ነውና።

24ጥመትን ከአፍህ አስወግድ፤

ብልሹ ንግግርም ከከንፈሮችህ ይራቅ።

25ዐይኖችህ በቀጥታ ይመልከቱ፤

ትክ ብለህም ፊት ለፊት እይ።

26የእግርህን ጐዳና አስተካክል፤4፥26 ወይም ተመልከት

የጸናውን መንገድ ብቻ ያዝ።

27ወደ ቀኝ ወደ ግራ አትበል፤

እግርህን ከክፉ ጠብቅ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

箴言 4:1-27

父亲的教诲

1孩子们啊,

你们要听从父亲的教诲,

留心学习,以便领悟,

2因为我给你们的训诲是美好的,

不可背弃我的教导。

3我年幼时在父亲身边,

是母亲唯一的宠儿。

4父亲教导我说:

“要牢记我的话,

遵守我的诫命,就必存活。

5你要寻求智慧和悟性,

不要忘记或违背我的吩咐。

6不可离弃智慧,智慧必护佑你;

你要热爱智慧,智慧必看顾你。

7智慧至上,要寻求智慧,

要不惜一切,求得悟性。

8高举智慧,她必使你受尊崇;

拥抱智慧,她必使你得尊荣。

9她必为你戴上华冠,

加上荣冕。”

10孩子啊,你要听从我的教导,

就必延年益寿。

11我已经指示你走智慧之道,

引导你行正确的路。

12你行走,必不受妨碍;

你奔跑,绝不会跌倒。

13你要持守教诲,不要松懈;

要守护好,因为那是你的生命。

14不要涉足恶人的道,

不要行走坏人的路;

15要避开,不可踏足,

要绕道而行。

16因为他们不作恶就无法入睡,

不绊倒人就无法安眠;

17他们吃的是邪恶饼,

喝的是残暴酒。

18义人的道路好像黎明的曙光,

越照越亮,直到大放光明。

19恶人的道路一片幽暗,

他们不知被何物绊倒。

20孩子啊,你要聆听我的吩咐,

侧耳听我的训言;

21不要让它们离开你的视线,

要牢记在心。

22因为得到它们就得到生命,

全身也必康健。

23要一丝不苟地守护你的心,

因为生命之泉从心中涌出。

24不讲欺诈之言,

不说荒谬的话。

25眼睛要正视前方,

双目要向前直看。

26要铺平脚下的路,

使所行之道稳妥。

27不可偏右偏左,

要远离恶事。