New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 21:1-46

ኢየሱስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ

21፥1-9 ተጓ ምብ – ማር 11፥1-10፤ ሉቃ 19፥29-38

21፥4-9 ተጓ ምብ – ዮሐ 12፥12-15

1ኢየሩሳሌም መቃረቢያ ደብረ ዘይት ተራራ ላይ ወደምትገኘው ቤተ ፋጌ ወደተባለችው ስፍራ እንደ ደረሱ፣ ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤ 2እንዲህ አላቸው “ባቅራቢያችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፤ እንደ ደረሳችሁም አንዲት አህያ ከነውርንጫዋ ታስራ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም ወደ እኔ አምጧቸው። 3ማንም ሰው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ቢላችሁ፣ ‘ጌታ ይፈልጋቸዋል’ በሉት፤ ወዲያውኑ ይሰዳቸዋል።”

4ይህ የሆነውም በነቢዩ እንዲህ በማለት የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው።

5“ለጽዮን ልጅ እንዲህ በሏት፤

‘እነሆ፤ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፣

በአህያዪቱና በግልገሏ፣

በውርንጫዪቱም ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።’ ”

6ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ። 7አህያዪቱንና ውርንጫዋን አምጥተው ልብሶቻቸውን በላያቸው ላይ አኖሩ፤ እርሱም ተቀመጠባቸው። 8ከሕዝቡም አብዛኛው ልብሶቻቸውን፣ በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎቹም ከዛፎች ቅርንጫፍ እየዘነጠፉ በመንገዱ ላይ ጣል ጣል አደረጉ። 9ቀድሞት ከፊቱ የሚሄደውና ከኋላው ይከተለው የነበረው ሕዝብም እንዲህ እያለ ይጮኽ ነበር፣

“ሆሣዕና21፥9 በዕብራይስጡ አገላለጽ አሁን አድን! ማለት ሲሆን የምስጋና አገላለጽ ነው፤ ቍ 15 ይመ ለዳዊት ልጅ፤”

“በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤”

“ሆሣዕና በአርያም!”

10ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜም ከተማዋ በመላ፣ “ይህ ማነው?” በማለት ታወከች።

11ሕዝቡም፣ “ይህ በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት የመጣው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” አሉ።

ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲነግዱ ያገኛቸውን አስወጣቸው

21፥12-16 ተጓ ምብ – ማር 11፥15-18፤ ሉቃ 19፥45-47

12ከዚያም ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይሸጡና ይገዙ የነበሩትን አባረራቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ በመገለባበጥ፣ 13“ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን፣ ‘የዘራፊዎች ዋሻ’ አደረጋችሁት” አላቸው።

14በቤተ መቅደሱም ውስጥ ዐይነ ስውሮችና ሽባዎች ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እርሱም ፈወሳቸው። 15ነገር ግን የካህናት አለቆችና የኦሪት ሕግ መምህራን ያደረጋቸውን ታምራትና፣ “ሆሣዕና፤ ለዳዊት ልጅ” እያሉ የሚጮኹትን ሕፃናት ባዩ ጊዜ በቍጣ ተሞሉ።

16እነርሱም፣ “እነዚህ ሕፃናት የሚሉትን ትሰማለህ” አሉት።

ኢየሱስም፣ “አዎን እሰማለሁ፤ እንዲህ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?”

“ ‘ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ፣

ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ።’ ”

17ትቶአቸው ከከተማው ወጣ፤ ወደ ቢታንያም ሄዶ በዚያው አደረ።

ፍሬ አልባ የሆነችው በለስ

21፥18-22 ተጓ ምብ – ማር 11፥12-14፡20-24

18ኢየሱስ በማግስቱ ማለዳ ወደ ከተማዪቱ በመመለስ ላይ ሳለ ተራበ፤ 19በመንገድ ዳርም አንድ የበለስ ዛፍ አይቶ ወደ እርሷ ሲሄድ ከቅጠል በስተቀር ምንም ስላላገኘባት፣ “ከእንግዲህ ፍሬ አይኑርብሽ!” አላት፤ የበለሷ ዛፍ ወዲያውኑ ደረቀች።

20ደቀ መዛሙርቱም የሆነውን አይተው በመደነቅ፣ “የበለሷ ዛፍ እንዴት ባንዴ ልትደርቅ ቻለች?” አሉ።

21ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩ፣ በበለሷ ዛፍ ላይ የሆነውን ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ይህንን ተራራ፣ ‘ከዚህ ተነቅለህ ባሕር ውስጥ ግባ’ ብትሉት እንኳ ይሆናል፤ 22እምነት ካላችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።”

በኢየሱስ ሥልጣን ላይ የቀረበ ጥያቄ

21፥23-27 ተጓ ምብ – ማር 11፥27-33፤ ሉቃ 20፥1-8

23ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በማስተማር ላይ ሳለ፣ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ቀርበው፣ “ይህን ሁሉ ነገር የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ሥልጣንስ የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ጠየቁት።

24ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ መልሱን ብትነግሩኝ፣ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፤ 25የዮሐንስ ጥምቀት የመጣው ከየት ነበር? ከሰማይ ወይስ ከሰዎች?”

እነርሱም እርስ በርስ በመነጋገር እንዲህ ተባባሉ፤ “ ‘ከሰማይ ነው?’ ካልን ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ 26‘ከሰዎች ነው’ ካልን ደግሞ፣ ‘ሕዝቡ ዮሐንስን ነቢይ ነው’ ብሎ ስለሚያምን እንፈራለን።”

27ስለዚህ፣ “አናውቅም” ብለው ለኢየሱስ መለሱለት።

እርሱም፣ “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።

የመታዘዝ ትርጒም

28ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ምን ይመስላችኋል? ሁለት ወንዶች ልጆች ያሉት አንድ ሰው ነበረ፤ ወደ መጀመሪያው ልጁ ሄዶ፣ ‘ልጄ ሆይ፤ ዛሬ ወደ ወይኑ ቦታ ሄደህ ሥራ’ አለው።

29“ልጁም፣ ‘አልሄድም’ አለው፤ ኋላ ግን ተጸጽቶ ሄደ።

30“ወደ ሁለተኛው ልጁ ሄዶ እንደዚያው አለው፤ ልጁም ‘እሺ ጌታዬ እሄዳለሁ’ አለው፤ ነገር ግን ሳይሄድ ቀረ።

31“ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?”

እነርሱም፣ “የመጀመሪያው ልጅ” አሉት።

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሟችኋል፤ 32መጥምቁ ዮሐንስ የጽድቅን መንገድ ሊያሳያችሁ ወደ እናንተ መጣ፤ እናንተ አላመናችሁትም፤ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ግን አመኑት። የሆነውን ካያችሁ በኋላ እንኳ ንስሓ ገብታችሁ አላመናችሁትም።

የወይን ዕርሻ ገበሬዎች ምሳሌ

21፥33-46 ተጓ ምብ – ማር 12፥1-12፤ ሉቃ 20፥9-19

33“ሌላም ምሳሌ ስሙ፤ አንድ የወይን ዕርሻ ባለቤት ነበረ፤ በዕርሻው ዙሪያ አጥር አጠረ፤ ለወይኑ መጭመቂያ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ለጥበቃ የሚሆን ማማ ሠራ፤ ከዚያም ዕርሻውን ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። 34የመከር ወራት ሲደርስ፣ ፍሬውን ለመቀበል አገልጋዮቹን ወደ ገበሬዎቹ ላካቸው።

35“ገበሬዎቹም አገልጋዮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት። 36እርሱም ከፊተኞቹ የሚበልጡ ሌሎች አገልጋዮቹን ላከ፤ ገበሬዎቹም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው። 37በመጨረሻም፣ ‘ልጄን ያከብሩታል’ በማለት ልጁን ላከ።

38“ነገር ግን ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ፣ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ። 39ይዘውም ከወይኑ ዕርሻ ውጭ አውጥተው ገደሉት።

40“ታዲያ የወይኑ ዕርሻ ባለቤት ሲመጣ እነዚያን ገበሬዎች ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል?”

41እነርሱም፣ “እነዚያን ክፉዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ከወይኑ ዕርሻ ተገቢውን ፍሬ በወቅቱ ለሚያስረክቡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።

42ኢየሱስም እንዲህ ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈውን አላነበባችሁምን? አላቸው፤

“ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣

የማእዘን ራስ21፥42 ወይም የማእዘን ድንጋይ ሆነ፤

እግዚአብሔር ይህን አድርጎአል፤

ሥራውም ለዐይናችን ድንቅ ነው።’

43“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ተወስዳ ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች፤ 44በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል፤ ድንጋዩ የሚወድቅበት ሰው ግን ይደቅቃል።”21፥44 አንዳንድ ቅጆች ቍጥር 44 የላቸውም

45የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፣ ስለ እነርሱ የሚናገር መሆኑን ዐወቁ። 46ነገር ግን ይዘው ሊያስሩት ቢፈልጉም ሕዝቡ ኢየሱስን እንደ ነቢይ አድርጎ ይመለከት ስለ ነበር ፈሩ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

馬太福音 21:1-46

光榮進聖城

1耶穌和門徒離耶路撒冷越來越近了,他們來到橄欖山旁的伯法其2耶穌派兩個門徒進村,並對他們說:「你們到前面的村莊去,就會看見一頭母驢拴在那裡,旁邊還有一頭驢駒。你們把牠們解開,牽到我這裡。 3要是有人問起,你們就說,『主要用牠們』,那人會立刻讓你們牽來。」 4這件事是要應驗先知的話:

5「要對錫安21·5 」希伯來文是「女子」,可能是對錫安的暱稱。說,『看啊,你的君王來了!祂謙卑地騎著驢,騎著一頭驢駒。』」

6兩個門徒照著耶穌的吩咐去了, 7把母驢和驢駒帶了回來。他們把自己的衣服蓋在驢背上,讓耶穌騎上去。 8許多人把衣服鋪在路上,也有些人砍下樹枝鋪在路上。 9眾人前呼後擁,歡呼著說:

「和散那21·9 和散那」原意是「拯救我們」,此處有「讚美」的意思。歸於大衛的後裔!

奉主名來的當受稱頌!

和散那歸於至高之處的上帝!」

10耶穌進耶路撒冷時,全城轟動,說:「這是誰?」

11眾人說:「祂是先知耶穌,來自加利利拿撒勒。」

潔淨聖殿

12耶穌進入聖殿,趕走裡面做買賣的人,又推翻兌換錢幣之人的桌子和賣鴿子之人的凳子。

13耶穌斥責他們說:「聖經上說,『我的殿必稱為禱告的殿。』你們竟把它變成了賊窩。」

14殿中的瞎子和瘸子都來到耶穌面前,祂便醫好了他們。 15祭司長和律法教師看見祂所行的奇事,又聽見小孩子在聖殿裡高聲喊著:「和散那歸於大衛的後裔!」便十分惱怒。 16他們責問耶穌說:「你聽見這些人說的了嗎?」

耶穌說:「我聽見了。聖經上說,『你使孩童和嬰兒口中發出頌讚』,你們沒有讀過嗎?」 17然後,祂便離開他們,出城前往伯大尼,在那裡住宿。

咒詛無花果樹

18清早,耶穌在回城的途中餓了。 19祂看見路旁有一棵無花果樹,便走過去,卻發現除了葉子外什麼也沒有。

祂對那棵樹說:「你將再不會結果子!」那棵樹立刻枯萎了。

20門徒見了就驚奇地問:「這棵樹怎麼一下子枯萎了?」

21耶穌回答說:「我實在告訴你們,如果你們有信心、不懷疑,不但能使無花果樹枯乾,就算對這座山說,『從這裡挪開,投進大海裡!』也照樣可以實現。 22所以,你們禱告時無論求什麼,只要有信心,就必定得到。」

質問耶穌的權柄

23耶穌進了聖殿,正在教導人的時候,祭司長和民間的長老來質問祂:「你憑什麼權柄做這些事?誰授權給你了?」

24耶穌說:「我也要問你們一個問題,你們回答了,我就告訴你們我憑什麼權柄做這些事。 25約翰的洗禮是從哪裡來的?從天上來的,還是從人來的?」

他們便彼此議論說:「如果我們說『是從天上來的』,祂一定會問我們,『那你們為什麼不信他?』 26但如果我們說『是從人來的』,又怕觸怒百姓,因為他們相信約翰是個先知。」 27於是,他們回答耶穌說:「我們不知道。」

耶穌說:「我也不告訴你們我憑什麼權柄做這些事。」

兩個兒子的比喻

28耶穌又說:「你們怎樣看這件事?某人有兩個兒子。他對大兒子說,『孩子,你今天到葡萄園工作吧!』

29「大兒子回答說,『我不去!』但後來他改變了主意,就去了。

30「那父親又對小兒子說,『你今天到葡萄園工作吧!』小兒子回答說,『好的,父親。』他答應了,卻沒有去。

31「你們認為這兩個兒子,到底哪一個服從父親呢?」

他們回答道:「大兒子。」

耶穌說:「我實在告訴你們,稅吏和娼妓要比你們先進上帝的國。 32因為約翰來指示你們當行的正路,你們不信他,但稅吏和娼妓信了。你們親眼看見了這些事,竟然還是執迷不悟,不肯信他。

惡毒的佃戶

33「你們再聽一個比喻。有個園主栽種了一個葡萄園,在園子的四周建造圍牆,又在園中挖了一個榨酒池,建了一座瞭望臺,然後把葡萄園租給佃戶,就出遠門了。 34到了收穫的季節,園主派奴僕到佃戶那裡收果子。 35但那些佃戶卻抓住他的奴僕,打傷一個,殺死一個,又用石頭打死了一個。 36於是,園主又派更多的奴僕去,結果也遭到同樣的對待。 37最後,園主派了自己的兒子去,心想,『他們肯定會尊重我的兒子。』 38然而,那些佃戶看見園主的兒子來了,就商量說,『這是園主的繼承人。來吧!我們殺掉他,佔了他的產業!』 39於是,他們抓住他,把他推出園外殺了。 40那麼,當園主回來的時候,他會怎樣處置那些佃戶呢?」

41他們說:「他會毫不留情地除掉那些惡人,然後把葡萄園租給其他按時交果子的佃戶。」

42耶穌說:

「『工匠丟棄的石頭已成了房角石。

這是主的作為,在我們看來奇妙莫測。』

你們難道沒有讀過這段經文嗎? 43所以,我告訴你們,將把上帝的國從你們那裡奪去,賜給結果子的人。 44凡跌在這石頭上的人,一定粉身碎骨;這石頭落在誰身上,就會把誰砸爛。」

45祭司長和法利賽人聽了耶穌的比喻,明白是針對他們講的。 46他們試圖逮捕耶穌,但又害怕百姓,因為百姓都認為耶穌是先知。