New Amharic Standard Version

ሚክያስ 5:1-15

ከቤተ ልሔም ገዥ እንደሚመጣ የተሰጠ ተስፋ

1አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤

ጭፍሮችሽን አሰልፊ5፥1 ወይም አንቺ የተቀጠርሽ ከተማ ሆይ፤ ቅጥርሽን አጥብቂ

ከበባ ተደርጎብናልና፤

የእስራኤልን ገዥ፣

ጒንጩን በበትር ይመቱታል።

2“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤

ከይሁዳ ነገዶች5፥2 ወይም ገዦች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣

አመጣጡ5፥2 ወይም ከቀድሞ ቀናት ከጥንት፣

ከቀድሞ ዘመን5፥2 ዕብራይስጡ አወጣጡ ይላል ወይም ከዘላለም የሆነ የሆነ፣

የእስራኤል ገዥ፣

ከአንቺ ይወጣልኛል።”

3ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣

እስራኤል ትተዋለች፤

የተቀሩት ወንድሞቹም፣

ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ።

4በእግዚአብሔር ኀይል

በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣

ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል።

በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣

ተደላድለው ይኖራሉ።

5እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።

ትድግናና ጥፋት

አሦራዊ ምድራችንን ሲወር፣

ምሽጐቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣

ሰባት እረኞችን፣

እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።

6የአሦርን ምድር በሰይፍ፣

የናምሩድን ምድር5፥6 ወይም ናምሩድን በመግቢያው በር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ5፥6 ወይም ያፈርሳሉ

አሦራዊው ምድራችንን ሲወር፣

ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣

እርሱ ነጻ ያወጣናል።

7የያዕቆብ ትሩፍ፣

በብዙ አሕዛብ መካከል

ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣

በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣

ሰውን እንደማይጠብቅ፣

የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል።

8በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣

በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣

የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣

በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣

እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣

የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።

9እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤

ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።

10“በዚያን ጊዜ” ይላል እግዚአብሔር፤

“ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤

ሠረገሎቻችሁን እደመስሳለሁ።

11የምድራችሁን ከተሞች እደመስሳለሁ፤

ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ።

12ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤

ከእንግዲህም አታሟርቱም።

13የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣

የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤

ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራ

አትሰግዱም።

14የአሼራ ምስልን ዐምድ5፥14 አሼራ የተባለችው አምላክ ትእምርት ነው። ከመካከላችሁ እነቅላለሁ፤

ከተሞቻችሁንም እደመስሳለሁ።

15ያልታዘዙኝን አሕዛብ፣

በቍጣና በመዓት እበቀላቸዋለሁ።”

Korean Living Bible

미가 5:1-15

베들레헴에서 탄생하실 메시아

1이스라엘 사람들아, 병력을 동원하라. 우리가 포위되었으니 원수들이 막대기 로 이스라엘 통치자의 뺨을 칠 것이다.

2여호와께서 말씀하신다. “베들레헴 에브라다야, 너는 유다에서 가장 작은 마을 중의 하나이지만 너에게서 이스라엘을 다스릴 자가 나올 것이다. 5:2 또는 ‘그의 근본은 상고에, 태초에니라’그는 영원 전부터 있는 자이다.”

35:3 또는 ‘임산한 여인이 해산하기까지’이스라엘의 수난이 끝날 때까지 하나님이 자기 백성을 이방인들의 손에 맡겨 두실 것이며 그 후에 5:3 또는 ‘그 형제 남은 자가’흩어져 있는 그의 동족들이 이스라엘 땅으로 돌아올 것이다.

4그가 오면 여호와의 능력과 그의 하나님 여호와의 위엄으로 자기 백성을 다스리고 그들을 안전하게 살게 할 것이다. 이것은 온 세상 사람들이 그의 위대함을 인정하고

5그는 우리의 평화가 될 것이기 때문이다.

이스라엘의 원수들에 대한 심판

앗시리아 사람들이 우리 땅을 침략하여 우리 요새로 쳐들어오면 우리는 5:5 원문에는 ‘일곱 목자 와 여덟 군왕을’많은 강력한 지도자들을 보내 그들과 싸울 것이다.

6그 지도자들이 칼로 니므롯 땅 앗시리아를 다스릴 것이다. 앗시리아 사람들이 우리 땅을 침략할 때 5:6 원문에는 ‘그가’그들이 우리를 앗시리아 사람의 손에서 구해 낼 것이다.

7그때 살아 남은 이스라엘 민족은 여호와께서 내리시는 이슬 같고 풀잎에 내리는 단비 같을 것이며 그들은 하나님을 의지하고 사람을 의지하지 않을 것이다.

8그들은 온 세계에 흩어져 살게 될 것이며 숲이나 목장에서 먹이를 찾는 사자와 같아서 한번 지나가면 마구 부수고 짓밟아 버릴 것이므로 피할 자가 없을 것이다.

9이스라엘은 그 원수들을 정복하여 그들을 완전히 멸망시킬 것이다.

10여호와께서 말씀하신다. “그 때에 내가 너희 말들을 없애 버리고 너희 전차들을 부숴 버리며

11너희 성들을 파괴하고 너희 요새들을 무너뜨릴 것이다.

12내가 너희 마법을 없애 버리겠다. 너희 가운데 다시는 점쟁이가 없을 것이다.

13내가 너희 모든 우상을 없애 버릴 것이니 너희가 다시는 손으로 만든 것을 섬기지 않을 것이다.

14내가 또 너희 가운데서 아세라 여신상을 뿌리째 뽑아 버리고 너희 성들을 파괴할 것이며

15나에게 순종하지 않은 모든 나라에 내 분노를 쏟아 보복할 것이다.”