መዝሙር 99 NASV - 诗篇 99 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 99:1-9

መዝሙር 99

ጻድቅና ቅዱስ አምላክ

1እግዚአብሔር ነገሠ፤

ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤

በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጦአል፤

ምድር ትናወጥ።

2እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤

ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ብሎአል።

3ታላቁንና አስፈሪውን ስምህን ይወድሱ፤

እርሱ ቅዱስ ነው።

4ፍትሕን የምትወድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤

አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤

ፍትሕንና ቅንነትንም፣

ለያዕቆብ አደረግህ።

5አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤

በእግሩ መርገጫ ስገዱ፤

እርሱ ቅዱስ ነውና።

6ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤

ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤

እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ፤

እርሱም መለሰላቸው።

7ከደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው፤

እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ።

8እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤

አንተ መለስህላቸው፤

ጥፋታቸውን99፥8 ወይም የተፈጸመባቸውን በደል ማለት ነው። ብትበቀልም እንኳ፣

አንተ ይቅር የምትላቸው አምላክ ነህ።

9አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤

በቅዱስ ተራራውም ላይ ስገዱ፤

አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 99:1-9

第 99 篇

上帝是圣洁的君王

1耶和华掌权,万民当战抖;

祂坐在基路伯天使之上,

大地当战抖。

2耶和华在锡安伟大无比,

超越万邦。

3万国要赞美你伟大而可畏的名,

你是圣洁的。

4你是大能的君王,

喜爱正义,维护公平,

雅各家秉公行义。

5要尊崇我们的上帝耶和华,

俯伏在祂脚凳前敬拜,

祂是圣洁的。

6祂的祭司中有摩西亚伦

呼求祂的人中有撒母耳

他们求告耶和华,

祂就应允他们。

7祂在云柱中向他们说话,

他们遵守祂赐下的法度和律例。

8耶和华,我们的上帝啊,

你应允了他们,

向他们显明你是赦罪的上帝,

但也惩罚他们的罪恶。

9要尊崇我们的上帝耶和华,

在祂的圣山上敬拜祂,

因为我们的上帝耶和华是圣洁的。