መዝሙር 91 NASV - 诗篇 91 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 91:1-16

መዝሙር 91

የእግዚአብሔር ጥበቃ

1በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣

ሁሉን በሚችል አምላክ91፥1 በዕብራይስጥ ሻዳይ ማለት ነው። ጥላ ሥር ያድራል።

2እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣

የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።91፥2 አንዳንድ ትርጒሞች ይላል ይላሉ።

3እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣

ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።

4በላባዎቹ ይጋርድሃል፤

በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤

ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።

5የሌሊትን አስደንጋጭነት፣

በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤

6በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣

በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም።

7በአጠገብህ ሺህ፣ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃል፤

ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

8በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤

የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ።

9እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣

ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።

10ክፉ ነገር አያገኝህም፤

መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤

11በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣

መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋልና።

12እግርህ ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣

በእጆቻቸው ወደ ላይ ያነሡሃል።

13በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤

ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

14“ወዶኛልና እታደገዋለሁ፤

ስሜን አውቆአልና እከልለዋለሁ።

15ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤

በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤

አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።

16ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤

ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 91:1-16

第 91 篇

上帝是我们的保护者

1安居在至高者隐秘处的人,

必蒙全能者的荫庇。

2我要对耶和华说:

“你是我的避难所,我的堡垒,是我所信靠的上帝。”

3祂必救你脱离猎人的网罗和致命的瘟疫。

4祂必用祂的羽毛遮盖你,

用祂的双翼保护你,

祂的信实是你的盾牌和壁垒。

5你必不惧怕黑夜的恐怖,

或白日的飞箭,

6或黑暗中横行的瘟疫,

或正午肆虐的灾难。

7尽管千人扑倒在你左边,

万人扑倒在你右边,

你必安然无恙。

8你必亲眼目睹恶人受惩罚。

9因为你以至高者耶和华——我的避难所作你的居所,

10祸患不会临到你身上,

灾难不会靠近你的住处。

11因为祂必命令祂的天使随时随地保护你。

12天使会用手托住你,

不让你的脚碰在石头上。

13你必将狮子和毒蛇踩在脚下,

你必践踏猛狮和巨蛇。

14耶和华说:“因为他爱我,我必拯救他;

因为他信靠我的名,

我必保护他。

15他求告我,我就答应他;

他遭遇患难,我必与他同在。

我必拯救他,赐他尊贵的地位。

16我必赐他长寿,

并让他看见我的拯救之恩。”