መዝሙር 90 NASV - 诗篇 90 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 90:1-17

አራተኛ መጽሐፍ

ከመዝሙር 90–106

መዝሙር 90

የሰው ልጅ ሕይወት

የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት

1እግዚአብሔር ሆይ፤

አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን።

2ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣

ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣

አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።

3ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤

“የሰው ልጆች ሆይ፤ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ” ትላለህ፤

4ሺህ ዓመት በፊትህ፣

እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣

እንደ ሌሊትም እርቦ ነውና።

5እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበናሉ፤

እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤

6ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤

ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል።

7በቊጣህ አልቀናልና፤

በመዓትህም ደንግጠናል።

8በደላችንን በፊትህ፣

የተሰወረ ኀጢአታችንንም በገጽህ ብርሃን ፊት አኖርህ።

9ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ዐልፎአልና፤

ዕድሜአችንንም በመቃተት እንጨርሳለን።

10የዕድሜአችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤

ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤

ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጒዳለን።

11የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል?

መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው።

12ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣

ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን።

13እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል?

ለአገልጋዮችህም ራራላቸው።

14በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣

ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን።

15መከራ ባሳየኸን ዘመን መጠን፣

ክፉም ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሰኘን።

16ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣

ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ።

17የጌታ የአምላካችን ሞገስ90፥17 ውበት ለማለት ነው። በላያችን ይሁን፤

የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን፤

አዎን፣ ፍሬያማ አድርግልን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 90:1-17

卷四:诗篇90—106

第 90 篇

上帝与世人

上帝的仆人摩西的祈祷。

1主啊,

你是我们世世代代的居所。

2群山尚未诞生,

大地和世界还未形成,

从亘古到永远,你是上帝。

3你叫人归回尘土,

说:“世人啊,归回尘土吧。”

4在你眼中,

千年如一日,又如夜里的一更。

5你像急流一般把世人冲走,

叫他们如梦消逝。

他们像清晨的嫩草,

6清晨还生机盎然,

傍晚就凋谢枯萎。

7你的怒气使我们灭亡,

你的愤怒使我们战抖。

8你知道我们的罪恶,

对我们隐秘的罪了如指掌。

9我们活在你的烈怒之下,

一生就像一声叹息飞逝而去。

10我们一生七十岁,

强壮的可活八十岁,

但人生最美好的时光也充满劳苦和愁烦,

生命转瞬即逝,

我们便如飞而去。

11谁明白你愤怒的威力?

有谁因为明白你的烈怒而对你心存敬畏呢?

12求你教导我们明白人生有限,

使我们做有智慧的人。

13耶和华啊,我还要苦候多久呢?

求你怜悯你的仆人。

14求你在清晨以慈爱来满足我们,

使我们一生欢喜歌唱。

15你使我们先前经历了多少苦难和不幸的岁月,

求你也赐给我们多少欢乐的岁月。

16求你让仆人们看见你的作为,

让我们的后代看见你的威荣。

17愿主——我们的上帝恩待我们,

使我们所做的亨通,

使我们所做的亨通。