መዝሙር 82 NASV - 诗篇 82 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 82:1-8

መዝሙር 82

ሙሱናን ዳኞች

የአሳፍ መዝሙር

1እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ መካከል ተሰየመ፤

በአማልክትም ላይ ይፈርዳል፤ እንዲህም ይላል፦

2“ፍትሕን የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው?

ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው? ሴላ

3ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ አደጎች ፍረዱላቸው፤

የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ።

4ወገን የሌለውንና ችግረኛውን ታደጉ፤

ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።

5“ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤

በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤

የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።

6“እኔም፤ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤

ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ’ አልሁ።

7ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤

እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።”

8አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ በምድር ላይ ፍረድ፤

ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 82:1-8

第 82 篇

斥责不公正的审判

亚萨的诗。

1上帝站在天庭的会中,

向众神明宣布祂的判决,

2说:“你们不秉公行义,

偏袒恶人要到何时呢?(细拉)

3你们要为穷人和孤儿主持公道,

为贫寒和受压迫的人伸张正义。

4要救助穷苦的人,

使他们脱离恶人的欺压。

5你们愚昧无知,

行在黑暗中,

大地的根基摇动。

6我曾说你们都是神,

都是至高者的儿子,

7但你们要跟世人一样死去,

像人间的王侯一样灭亡。”

8上帝啊,求你起来审判世界,

因为世上的万国都属于你。