መዝሙር 81 NASV - 诗篇 81 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 81:1-16

መዝሙር 81

ለዳስ በዓል የሚዜም ቅኔ

ለመዘምራን አለቃ፤ በዋሽንት የሚዜም፣ የአሳፍ መዝሙር

1ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ፤

ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ።

2ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤

በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ።

3በሙሉ ጨረቃ፣ በክብረ በዓላችን ዕለት፣

በወሩ መግቢያ፣ ጨረቃ ስትወለድ መለከት ንፉ፤

4ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ሥርዐት፣

የያዕቆብም አምላክ ድንጋጌ ነውና።

5ሙሉ ለሙሉ ግብፅን ለቆ በወጣ ጊዜ፣

ይህን ለዮሴፍ ደነገገለት፤

በማላውቀውም81፥5 አንዳንዶች የማናውቀውን ድምፅ ሰማን ይላሉ። ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦

6“ትከሻውን ከሸክም ገላገልሁት፤

እጁንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ።

7በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግሁህ፤

በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ፤

በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ። ሴላ

8“ሕዝቤ ሆይ፤ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ፤

እስራኤል ሆይ፤ ምነው ብታደምጠኝ!

9በአንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አይኑር፤

ለሌላም አምላክ አትስገድ።

10ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣

እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤

አፍህን በሰፊው ክፈተው፤ እኔም እሞላዋለሁ።

11“ሕዝቤ ግን አላደመጠኝም፤

እስራኤልም እጅ አልሰጥ አለኝ።

12ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣

አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው።

13“ምነው ሕዝቤ ቢያደምጠኝ ኖሮ፣

እስራኤል በመንገዴ በሄደ ኖሮ፣

14ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባንበረከክኋቸው ነበር፤

እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ ባነሣሁ ነበር።

15እግዚአብሔርን የሚጠሉ በፊቱ ይርዳሉ፤

ቅጣታቸውም እስከ ዘላለም የሚዘልቅ ነው።

16እናንተን ግን ምርጡን ስንዴ አበላችኋለሁ፤

ከዐለቱም ማር አጠግባችኋለሁ።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 81:1-16

第 81 篇

歌颂上帝的恩惠

亚萨的诗,交给乐长,用迦特乐器。

1要歌颂赐我们力量的上帝,

雅各的上帝欢呼。

2要唱诗,击鼓,弹起琴瑟。

3要在我们过节的朔日和望日81:3 朔日和望日”即每月的初一和十五。吹响号角。

4这是以色列的律例,

雅各的上帝所定的法令。

5上帝攻击埃及的时候,

约瑟立下此法度。

我在那里听见陌生的声音说:

6“我卸下了你肩上的重担,

使你的双手不再做苦工,

7你在苦难中向我呼求,

我就拯救了你,

从雷声隆隆的密云中应允了你。

我在米利巴泉边考验你。(细拉)

8我的子民啊,

要听我的警告。

以色列人啊,

但愿你们听从我的话。

9你们断不可供奉别的神明,

也不可向外族的神明下拜,

10我是你们的上帝耶和华,

曾把你们带出埃及

张开你们的口吧,

我必使你们饱足。

11我的子民却不肯听我的话,

以色列不愿意顺从我。

12因此我就任凭他们顽固不化,

为所欲为。

13但愿我的子民肯听从我,

以色列人肯遵行我的道。

14那时,我必迅速制服他们的敌人,

伸手攻击他们的仇敌。

15憎恶我的人要在我面前屈膝投降,永远沉沦。

16我要以上好的麦子供养我的子民,

让他们饱享磐石间的蜂蜜。”