መዝሙር 80 NASV - 诗篇 80 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 80:1-19

መዝሙር 80

ለእስራኤል ተሐድሶ የቀረበ ጸሎት

ለመዘምራን አለቃ፤ “የኪዳን ጽጌረዳ” በሚለው ቅኝት የሚዜም፤ የአሳፍ መዝሙር

1ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣

የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤

በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፤

በብርሃንህ ተገለጥ፤

2በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይ።

ኀይልህን አንቀሳቅስ፤

መጥተህም አድነን።

3አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤

እንድንም ዘንድ፣

ፊትህን አብራልን።

4የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤

በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነደው፣

እስከ መቼ ድረስ ነው?

5የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤

ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።

6ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤

ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን።

7የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤

እንድንም ዘንድ፣

ፊትህን አብራልን።

8ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ፤

አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት።

9መሬቱን መነጠርህላት፤

እርሷም ሥር ሰዳ አገሩን ሞላች።

10ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤

ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።

11ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣80፥11 ሜድትራኒያን ሳይሆን አይቀርም።

ቊጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ80፥11 የኤፍራጥስ ወንዝ ለማለት ነው። ዘረጋች።

12ታዲያ ዐላፊ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲለቅም፣

ለምን ቅጥሯን አፈረስህ?

13ዕርያ ከዱር ወጥቶ ያበለሻሻታል፤

በሜዳ የሚንጋጋ እንስሳ ሁሉ ይበላታል።

14የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤

ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤

ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤

15ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ቡቃያ፣

ለራስህ ያጸደቅሃት ተክል80፥15 ወንድ ልጅ የሚሉ ትርጒሞች አሉ። ናት።

16እርሷም በእሳት ተቃጥላለች፤

የግንባርህ ተግሣጽ ያጠፋቸዋል።

17ለራስህ ባበረታኸው የሰው ልጅ ላይ፣

በቀኝ እጅህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን።

18ከእንግዲህ አንተን ትተን ወደ ኋላ አንመለስም፤

ሕያዋን አድርገን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን።

19የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልሰን፤

እንድንም ዘንድ፣

ፊትህን አብራልን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 80:1-19

第 80 篇

为国家复兴祈求

亚萨的诗,交给乐长,调用“作证的百合花”。

1-2以色列的牧者啊,

你像照顾羊群一样带领约瑟的子孙,

求你垂听我们的祈祷。

坐在基路伯天使之上的耶和华啊,

求你向以法莲便雅悯玛拿西发出光辉,

求你施展大能来拯救我们。

3上帝啊,求你复兴我们,

用你脸上的荣光照耀我们,

使我们得救。

4万军之上帝耶和华啊,

你因你子民的祷告而发怒,

要到何时呢?

5你使我们以泪洗面,

以哀伤果腹,

6又使我们成为邻国争夺的对象,

仇敌都嘲笑我们。

7万军之上帝啊,

求你复兴我们,

用你脸上的荣光照耀我们,

使我们得救。

8你从埃及带出一棵葡萄树,

赶走外族人,把它栽种起来。

9你为它开垦土地,

它就扎根生长,布满这片土地。

10它的树荫遮盖群山,

枝子遮蔽香柏树。

11它的枝条延伸到地中海,

嫩枝伸展到幼发拉底河。

12你为何拆毁了它的篱笆,

让路人随意摘取葡萄呢?

13林中的野猪蹂躏它,

野兽吞吃它。

14万军之上帝啊,

求你回来,

求你在天上垂顾我们这棵葡萄树,

15这棵你亲手栽种和培育的葡萄树。

16这树被砍倒,被焚烧,

愿你发怒毁灭仇敌。

17求你扶持你所拣选的人,你为自己所养育的人。

18我们必不再背弃你,

求你复兴我们,

我们必敬拜你。

19万军之上帝耶和华啊,

求你复兴我们,

用你脸上的荣光照耀我们,

使我们得救。