መዝሙር 74 NASV - 诗篇 74 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 74:1-23

መዝሙር 74

ስለ መቅደሱ መፍረስ የቀረበ ጸሎት

የአሳፍ ትምህርት

1አምላክ ሆይ፤ ለዘላለም የጣልኸን ለምንድን ነው?

በማሰማሪያህ ባሉ በጎችህስ ላይ ቍጣህ ለምን ነደደ?

2ጥንት ገንዘብህ ያደረግሃትን ጉባኤ፣

የዋጀሃትን የርስትህን ነገድ፣

መኖሪያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራ አስብ።

3እርምጃህን ለዘላለሙ ባድማ ወደ ሆነው አቅና፤

ጠላት በመቅደስህ ውስጥ ያለውን ሁሉ አበላሽቶአል።

4ጠላቶችህ በመገናኛ ስፍራህ መካከል ደነፉ፤

አርማቸውንም ምልክት አድርገው በዚያ አቆሙ።

5በጫካ መካከል ዛፎችን ለመቍረጥ፣

መጥረቢያ የሚያነሣ ሰው መሰሉ።

6በእደ ጥበብ ያጌጠውን ሥራ ሁሉ፣

በመጥረቢያና በመዶሻ ሰባበሩት።

7መቅደስህን አቃጥለው አወደሙት፤

የስምህንም ማደሪያ አረከሱ።

8በልባቸውም፣ “ፈጽሞ እንጨቍናቸዋለን” አሉ፤

እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ የተመለከበትን ስፍራ ሁሉ አቃጠሉ።

9የምናየው ምልክት የለም፤

ከእንግዲህ የሚነሣ አንድም ነቢይ የለም፤

ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል የሚያውቅ በእኛ ዘንድ የለም።

10አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚያሾፈው እስከ መቼ ነው?

ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?

11እጅህን ለምን ትሰበስባለህ?

ቀኝ እጅህን ለምን በብብትህ ሥር ታቆያለህ?

12አምላክ ሆይ፤ አንተ ከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነህ፤

በምድር ላይ ማዳንን አደረግህ።

13ባሕርን በኀይልህ የከፈልህ አንተ ነህ፤

የባሕሩንም አውሬ ራሶች በውሃ ውስጥ ቀጠቀጥህ።

14የሌዋታንን ራሶች አደቀቅህ፤

ለምድረ በዳ ፍጥረታትም ምግብ አድርገህ የሰጠሃቸው፣

15ምንጮችንና ፈሳሾችን ያፈለቅህ አንተ ነህ፤

ሳያቋርጡ የሚፈሱትንም ወንዞች አደረቅህ።

16ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው፤

ጨረቃንና ፀሓይን አንተ አጸናሃቸው።

17የምድርን ዳርቻ ሁሉ የወሰንህ አንተ ነህ፤

በጋውንም ክረምቱንም አንተ ሠራህ።

18እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣

ከንቱ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ አስብ።

19የርግብህን ነፍስ አሳልፈህ ለዱር አራዊት አትስጥ፤

የችግረኞች ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለሙ አትርሳ።

20ኪዳንህን አስብ፤

የዐመፅ መናኸሪያ በምድሪቱ ጨለማ ስፍራዎች ሞልተዋልና።

21የተጨቈኑት አፍረው አይመለሱ፤

ድኾችና ችግረኞች ስምህን ያመስግኑ።

22አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ ለዐላማህ ተሟገት፤

ከንቱ ሰው ቀኑን ሙሉ እንደሚያላግጥብህ አስብ።

23የባላጋራዎችህን ድንፋታ፣

ዘወትር የሚነሣውን የጠላቶችህን ፉከራ አትርሳ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 74:1-23

第 74 篇

祈求上帝眷顾祂的子民

亚萨的训诲诗。

1上帝啊,

你为何永远丢弃了我们?

你为何对自己草场上的羊大发雷霆?

2求你眷顾你在古时所救赎的子民,

你拣选为产业的族类,

求你眷顾你所居住的锡安山。

3求你前去观看那久已荒凉之地,

看看敌人对圣所的破坏。

4他们在你圣所中高声叫嚷,

竖立起自己的旗帜。

5他们大肆毁坏,

好像人抡起斧头砍伐树林。

6他们用斧头、锤子把雕刻的墙板都捣毁了。

7他们纵火焚烧你的圣所,

把它夷为平地,

亵渎了你的居所。

8他们心里说:“我们要彻底毁灭一切。”

于是他们烧毁了境内所有敬拜上帝的地方。

9我们再也看不到你的征兆,

先知也没有了。

无人知道这一切何时才会结束。

10上帝啊,

仇敌嘲笑你的名要到何时呢?

他们要永无休止地辱骂你吗?

11你为何不伸出大能的右手?

求你出手给他们致命的一击。

12上帝啊,

你自古以来就是我的王,

你给世上带来拯救。

13你曾用大能分开海水,

打碎水中巨兽的头。

14你曾打碎海怪的头,

把它丢给旷野的禽兽吃。

15你曾开辟泉源和溪流,

也曾使滔滔河水枯干。

16白昼和黑夜都属于你,

你设立了日月。

17你划定大地的疆界,

又创造了盛夏和寒冬。

18耶和华啊,

求你记住敌人对你的嘲笑和愚妄人对你的亵渎。

19求你不要把你的子民交给仇敌74:18-19 子民”希伯来文是“鸽子”;“仇敌”希伯来文是“野兽”。

不要永远对你受苦的子民弃置不顾。

20求你顾念你的应许,

因地上黑暗之处充满了暴力。

21求你不要让受压迫的人羞愧而去。

愿贫穷困苦的人赞美你的名。

22上帝啊,求你起来维护自己,

别忘记愚妄人怎样整天嘲笑你。

23不要对你仇敌的喧嚷置之不理,

与你为敌的人不停地叫嚣。