መዝሙር 72 NASV - 诗篇 72 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 72:1-20

መዝሙር 72

በተስፋ የሚጠባበቀው ንጉሥ

ስለ ሰሎሞን

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትህን ለንጉሥ፣

ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤

2እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤72፥2 ወይም እርሱ ሕዝቡን በጽድቅ ይዳኝ

ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል።

3ተራሮች ብልጽግናን፣

ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።

4ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤

የድኾችን ልጆች ያድናል፤

ጨቋኙንም ያደቀዋል።

5ፀሓይ እስካለች ድረስ፣

ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።72፥5 ወይም የተፈራ ይሆናል

6እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ ይወርዳል፤

እንደ ካፊያም ምድርን ያረሰርሳል።

7በዘመኑ ጽድቅ ይሰፍናል፤

ጨረቃ ከስፍራዋ እስከምትታጣ ድረስም ሰላም ይበዛል።

8ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣

ከታላቁም ወንዝ72፥8 የኤፍራጥስ ወንዝ ነው። እስከ ምድር ዳርቻ ይገዛል።

9የበረሓ ዘላኖች በፊቱ ይሰግዳሉ፤

ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ።

10የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣

ግብር ያመጡለታል፤

የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣

እጅ መንሻ ያቀርባሉ።

11ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤

ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል።

12ችግረኛው በጮኸ ጊዜ፣

ምስኪኑንና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል።

13ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤

ምስኪኖችንም ከሞት ያድናል።

14ሕይወታቸውን ከጭቈናና ከግፍ ያድናል፤

ደማቸውም በእርሱ ፊት ክቡር ነው።

15ዕድሜው ይርዘም!

ከዐረብ ወርቅ ይምጣለት፤

ዘወትር ይጸልዩለት፤

ቀኑንም ሙሉ ይባርኩት።

16በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤

በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ።

ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤

በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ።

17ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤

ዝናው ፀሓይ የምትኖረውን ዘመን ያህል ይዝለቅ፤

ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ይባረኩ፤

ሕዝቡ ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበለው።

18ብቻውን ድንቅ ነገር የሚያደርግ፣

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።

19ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ፤

ምድርም ሁሉ በክብሩ ይሞላ።

አሜን፤ አሜን።

20የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎት እዚህ ላይ ተፈጸመ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 72:1-20

第 72 篇

为君王祈祷

所罗门的诗。

1上帝啊,

求你将你的公正赐给王,

将你的公义赐给王的儿子。

2让他凭公义审判你的子民,

按公平对待那些贫苦的人。

3愿大山给百姓带来繁荣,

小山带来公义。

4愿他保护百姓中受苦的人,

拯救贫穷的人,打倒欺压者。

5只要日月尚存,

愿百姓永远敬畏你。

6愿他的统治如春雨降在新割过的草场上,

又像甘霖滋润大地。

7在他统治之下,

愿义人兴旺,国富民强,

如月长存。

8愿他的疆域横跨洋海,

幼发拉底河直到地极。

9愿旷野的居民都来向他下拜,

敌人都扑倒在尘土中。

10他施示巴西巴的君王都来纳贡称臣。

11愿君王都敬拜他,

万国都事奉他。

12贫穷人呼求,他便搭救;

困苦人无助,他就伸出援手。

13他怜悯软弱和贫困的人,

拯救贫困人的性命。

14他要救他们脱离别人的压迫和暴力,

因为他爱惜他们的生命。

15愿王寿命长久,

愿人们将示巴的金子献给他,

不断为他祷告,

终日称颂他。

16愿遍地五谷丰登,

山顶上出产丰富,

黎巴嫩的密林。

愿各城人口稠密如原野的青草。

17愿他的名流芳百世,如日长存。

愿万国都因他而蒙福,

都称颂他。

18以色列的上帝耶和华当受称颂,

唯有祂行奇妙的事。

19愿祂荣耀的名永受称颂!

愿普天下充满祂的荣耀。

阿们!阿们!

20耶西的儿子大卫的祷告结束。