መዝሙር 71 NASV - 诗篇 71 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 71:1-24

መዝሙር 71

የሽማግሌ ጸሎት

71፥1-3 ተጓ ምብ – መዝ 31፥1-4

1እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤

ከቶም አልፈር።

2በጽድቅህ ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤

ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም።

3ምንጊዜም የምሸሽበት፣

መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤

አንተ ዐለቴ ምሽጌ ነህና፣

ታድነኝ ዘንድ ትእዛዝህ ይውጣ።

4አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣

ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።

5ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፤

ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።

6ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤

ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤

አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ።

7ብዙዎች እንደ ጒድ አዩኝ፤

አንተ ግን ጽኑ አምባዬ ነህ።

8ቀኑን ሙሉ ክብርህን ያወራ ዘንድ፣

አፌ በምስጋናህ ተሞልቶአል።

9በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤

ጒልበቴም ባለቀበት ጊዜ አትተወኝ።

10ጠላቶቼ ተነጋግረውብኛልና፤

ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ በአንድ ላይ አሢረዋል፤

11እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ትቶታል፤

የሚያስጥለው የለምና፣ ተከታትላችሁ ያዙት” አሉ።

12አምላክ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤

አምላኬ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

13ባላንጣ የሆኑብኝ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤

ሊጐዱኝ የሚፈልጉ፣

ንቀትንና ውርደትን ይከናነቡ።

14እኔ ግን ሁል ጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፤

በምስጋና ላይ ምስጋና አቀርብልሃለሁ።

15አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣

ቀኑን ሙሉ ስለ ማዳንህ ይናገራል፤

ማቆሚያ ልኩንም አላውቅም።

16መጥቼ የጌታ እግዚአብሔርን ብርቱ ሥራ ዐውጃለሁ፤

የአንተን ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።

17አምላክ ሆይ፤ አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤

እኔም እስከ ዛሬ ድረስ ድንቅ ሥራህን ዐውጃለሁ።

18አምላክ ሆይ፤ ሳረጅና ስሸብትም አትተወኝ፤

ክንድህን ለመጭው ትውልድ፣

ኀይልህን ኋላ ለሚነሣ ሕዝብ ሁሉ፣

እስከምገልጽ ድረስ።

19አምላክ ሆይ፤ ጽድቅህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤

አንተ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፤

አምላክ ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?

20ብዙ መከራና ጭንቅ ብታሳየኝም፣

ሕይወቴን እንደ ገና ታድሳለህ፤

ከምድር ጥልቅም፣

እንደ ገና ታወጣኛለህ።

21ክብሬን ትጨምራለህ፤

ተመልሰህም ታጽናናኛለህ

22አምላኬ ሆይ፤ ስለ ታማኝነትህ፣

በበገና አመሰግንሃለሁ፤

የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፤

በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።

23ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤

አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።

24አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣

ቀኑን ሙሉ ያወራል፤

የእኔን መጐዳት የሚፈልጉ፣

አፍረዋልና፤ ተዋርደዋልም።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 71:1-24

第 71 篇

一个老年人的祈祷

1耶和华啊,我投靠了你,

求你使我永不蒙羞。

2求你凭公义搭救我,

侧耳听我的恳求,拯救我。

3求你成为保护我的磐石,

让我可以随时投靠你。

求你下令救我,

因为你是我的磐石和堡垒。

4我的上帝啊,

求你从恶人手中拯救我,

从邪恶、残暴之徒掌下拯救我。

5主耶和华啊,你是我的盼望,

我从小就信靠你。

6你使我出了母胎,

我从出生就依靠你,

我要永远赞美你。

7我的遭遇使许多人感到惊骇,

但你是我坚固的避难所。

8我口中充满对你的赞美,

终日述说你的荣耀。

9我年老时,求你不要丢弃我;

我体力衰微时,求你不要离弃我。

10我的仇敌议论我,

那些想杀害我的一起策划阴谋,说:

11“上帝已经丢弃了他。

去追赶、捉拿他吧,

因为无人会救他。”

12上帝啊,不要远离我;

我的上帝啊,求你快来帮助我!

13愿我的仇敌在羞辱中灭亡,

愿那些害我的人抱愧蒙羞。

14我必常常心怀盼望,

向你献上更多的赞美。

15虽然我无法测度你的公义和拯救之恩,

但我要终日传扬你的作为。

16主耶和华啊,

我要传扬你大能的作为,

单单述说你的公义。

17上帝啊,

我从小就受你的教导,

直到今日我仍传扬你奇妙的作为。

18上帝啊,

就是我年老发白的时候,

求你也不要丢弃我,

好让我把你的大能告诉下一代,世代相传。

19上帝啊,你的公义高达穹苍,

你成就了奇妙大事。

上帝啊,有谁能像你?

20你使我经历了许多患难,

最终必使我重获新生,

救我脱离死亡的深渊。

21你必赐我更大的尊荣,

你必再次安慰我。

22我的上帝啊,

我要弹琴赞美你的信实;

以色列的圣者啊,

我要伴随着琴声赞美你。

23你救赎了我的灵魂,

我的口和灵魂都要欢呼歌颂你。

24我要终日向人述说你的公义,

因为那些想害我的人已经蒙羞受辱。