መዝሙር 7 NASV - 诗篇 7 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 7:1-17

መዝሙር 7

በስደት ጊዜ የጻድቁ ሰው ጸሎት

ዳዊት በብንያማዊው በኩዝ ምክንያት ለእግዚአብሔር የዘመረው መዝሙር

1እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤

ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም፤

2አለበለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤

የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል።

3እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣

በደልም በእጄ ከተገኘ፣

4በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣

ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣

5ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ፤

ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል፤

ክብሬንም ከዐፈር ይደባልቅ። ሴላ

6እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤

በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤

አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!

7የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤

አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤

8እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል።

እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ፤

ልዑል ሆይ፤ እንደ ቅን አካሄዴ መልስልኝ።

9ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣

ጻድቅ አምላክ ሆይ፤

የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤

ጻድቁን ግን አጽና።

10ጋሻዬ7፥10 ወይም የኔ ልዑል ልዑል አምላክ ነው፤

እርሱ ልበ ቅኖችን ያድናቸዋል።

11እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤

ቍጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው።

12ሰው በንስሓ የማይመለስ ከሆነ ግን፣

ሰይፉን7፥12 ወይም ሰው ንስሓ ካልገባ፣ እግዚአብሔር ሰይፉን …  ይስላል፤

ቀስቱን ይገትራል።

13የሚገድሉ ጦር ዕቃዎቹን አሰናድቶአል፤

የሚንበለበሉትን ፍላጻዎቹንም አዘጋጅቶአል።

14ክፋትን እያማጠ ያለ ሰው፣

ቅጥፈትን አርግዞ፣ ሐሰትን ይወልዳል።

15ጒድጓድ ምሶ ዐፈሩን የሚያወጣ፣

ባዘጋጀው ጒድጓድ ራሱ ይገባበታል።

16ተንኰሉ ወደ ራሱ ይመለሳል፤

ዐመፃውም በገዛ ዐናቱ ላይ ይወርዳል።

17ስለ ጽድቁ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ፤

የልዑል እግዚአብሔርን ስም በመዝሙር አወድሳለሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 7:1-17

第 7 篇

求上帝伸张正义

大卫向耶和华唱的诗,与便雅悯人古实有关。

1我的上帝耶和华啊,我投靠你,

求你拯救我脱离追赶我的人。

2别让他们像狮子般撕裂我,

无人搭救。

3我的上帝耶和华啊,

倘若我犯了罪,

手上沾了不义;

4倘若我恩将仇报,

无故抢夺仇敌,

5就让仇敌追上我,

践踏我,使我声名扫地。(细拉)

6耶和华啊,

求你发怒攻击我暴怒的仇敌。

我的上帝啊,

求你来伸张正义。

7愿万民环绕你,

愿你从高天治理他们,

8愿你审判万民!

至高的耶和华啊,

我是公义正直的,

求你为我主持公道。

9鉴察人心肺腑的公义上帝啊,

求你铲除邪恶,扶持义人。

10上帝是我的盾牌,

祂拯救心地正直的人。

11上帝是公义的审判官,

天天向恶人发怒。

12他们若不悔改,祂必磨刀霍霍,

弯弓搭箭,诛灭他们。

13祂准备好了夺命的兵器,

火箭已在弦上。

14恶人心怀恶念,

居心叵测,滋生虚谎。

15他们挖了陷阱,却自陷其中。

16他们的恶行临到自己头上,

他们的暴力落到自己脑壳上。

17我要称谢耶和华的公义,

我要歌颂至高者耶和华的名。