መዝሙር 69 NASV - 诗篇 69 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 69:1-36

መዝሙር 69

እንጒርጒሮ

ለመዘምራን አለቃ፤ በ“ጽጌረዳ” ዜማ፤ የዳዊት መዝሙር

1አምላክ ሆይ፤ አድነኝ፤

ውሃ እስከ ዐንገቴ ደርሶብኛልና።

2የእግር መቆሚያ በሌለው፣

በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤

ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤

ሞገዱም አሰጠመኝ።

3በጩኸት ደከምሁ፤

ጉሮሮዬም ደረቀ፤

አምላኬን በመጠባበቅ፣

ዐይኖቼ ፈዘዙ።

4ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣

ከራሴ ጠጒር በዙ፤

ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣

በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤

ያልሰረቅሁትን ነገር፣

መልሰህ አምጣ ተባልሁ።

5እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤

በደሌም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

6ጌታ የሰራዊት አምላክ ሆይ፤

አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣

በእኔ ምክንያት አይፈሩ፤

የእስራኤል አምላክ ሆይ፤

አንተን አጥብቀው የሚሹ፣

ከእኔ የተነሣ አይዋረዱ።

7ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፤

እፍረትም ፊቴን ሸፍኖአልና።

8ለወንድሞቼ እንደ ባዕድ፣

ለእናቴም ልጆች እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።

9የቤትህ ቅናት በላችኝ፤

የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ዐርፎአል።

10ነፍሴን በጾም ባስመረርሁ ጊዜ፣

እነርሱ ሰደቡኝ።

11ማቅ በለበስሁ ጊዜ፣

መተረቻ አደረጉኝ።

12በቅጥሩ ደጅ ለሚቀመጡት የመነጋገሪያ ርእስ፣

ለሰካራሞችም መዝፈኛ ሆንሁ።

13እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በወደድኸው ሰዓት፣

ወደ አንተ እጸልያለሁ፤

አምላክ ሆይ፤ በታላቅ ምሕረትህ፣

በማዳንህም እርግጠኝነት መልስልኝ።

14ከረግረግ አውጣኝ፤

እሰጥም ዘንድ አትተወኝ፤

ከጥልቅ ውሃ፣

ከእነዚያ ከሚጠሉኝ ታደገኝ።

15ጐርፍ አያጥለቅልቀኝ፤

ጥልቅ ውሃም አይዋጠኝ፤

ጒድጓዱም ተደርምሶ አይዘጋብኝ።

16እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ በጎ ናትና ስማኝ፤

እንደ ርኅራኄም ብዛት መለስ በልልኝ።

17ፊትህን ከባሪያህ አትሰውር፤

ጭንቅ ውስጥ ነኝና ፈጥነህ መልስልኝ።

18ወደ እኔ ቀርበህ ታደገኝ፤

ስለ ጠላቶቼም ተቤዠኝ።

19የደረሰብኝን ስድብ፣ ዕፍረትና ውርደት ታውቃለህ፤

ጠላቶቼንም አንድ በአንድ ታውቃቸዋለህ።

20ስድብ ልቤን ጐድቶታል፤

ተስፋዬም ተሟጦአል፤

አስተዛዛኝ ፈለግሁ፤ አላገኘሁምም፤

አጽናኝም ፈለግሁ፤ አንድም አልነበረም።

21ምግቤን ከሐሞት ቀላቀሉ፤

ለጥማቴም ሆምጣጤ ሰጡኝ።

22የቀረበላቸው ማእድ ወጥመድ ይሁንባቸው፤

ለማኅበራቸውም አሽክላ ይሁን።

23ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፤

ጀርባቸውም ዘወትር ይጒበጥ።

24መዓትህን በላያቸው አፍስስ፤

የቍጣህም መቅሠፍት ድንገት ይድረስባቸው።

25ሰፈራቸው ባድማ ይሁን፤

በድንኳኖቻቸው የሚኖር አይገኝ፤

26አንተ የመታኻቸውን አሳደዋልና፤

ያቈሰልኻቸውንም ሥቃያቸውን አባብሰዋል።

27በበደላቸው በደል ጨምርባቸው፤

ወደ ጽድቅህም አይግቡ።

28ከሕይወት መጽሐፍ ይደምሰሱ፤

ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።

29ነገር ግን እኔ በሥቃይና በጭንቅ ላይ እገኛለሁ፤

አምላክ ሆይ፤ ማዳንህ ደግፎ ይያዘኝ።

30የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አወድሳለሁ፤

በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።

31ከበሬ ይልቅ፣

ቀንድና ጥፍር ካበቀለ እምቦሳም ይልቅ ይህ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።

32ድኾች ይህን ያያሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤

እናንተ እግዚአብሔርን የምትሹ ልባችሁ ይለምልም!

33እግዚአብሔር ችግረኞችን ይሰማልና፤

በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም።

34ሰማይና ምድር፣ ባሕርም፣

በውስጣቸውም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመስግኑት።

35እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፤

የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይሠራቸዋልና፤

ሕዝቡም በዚያ ይሰፍራል፤ ይወርሳታልም።

36የባሪያዎቹም ዘሮች ይወርሷታል፤

ስሙንም የሚወዱ በዚያ ይኖራሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 69:1-36

第 69 篇

祈求上帝拯救的祷告

大卫作的诗,交给乐长,调用“百合花”。

1上帝啊,求你拯救我,

因为洪水快把我淹没;

2我深陷泥沼,无法站稳脚;

我落入深渊,被洪流淹没。

3我连连呼救,已声嘶力竭;

我期盼上帝的帮助,望眼欲穿。

4无故恨我的人不计其数,

无故害我的仇敌势力强大,

逼我偿还我没有偷过的东西。

5上帝啊,你知道我的愚昧,

我的罪恶也瞒不过你。

6主——万军之耶和华啊,

求你不要使等候你的人因我而受辱;

以色列的上帝啊,

求你不要让信靠你的人因我而蒙羞。

7我为了你的缘故遭受辱骂,

羞辱满面。

8我的弟兄视我为陌生人,

我的手足看我为外人。

9我对你的殿充满炙热的爱,

辱骂你之人的辱骂都落在我身上。

10我悲伤禁食,

他们就羞辱我。

11我披上麻衣,

他们就讥笑我。

12我成了街谈巷议的话题,

醉汉作歌取笑我。

13可是,耶和华啊,

在你悦纳人的时候,

我向你祷告。

上帝啊,

求你以你的大爱和信实拯救我。

14求你救我脱离泥沼,

不要让我沉下去;

求你救我脱离恨我的人,

使我离开深渊。

15求你不要让洪水淹没我,

深渊吞灭我,

坟墓吞噬我。

16耶和华啊,求你答应我的祷告,

因为你充满慈爱和良善;

求你以无限的怜悯眷顾我。

17求你不要掩面不理你的仆人。

我正身陷困境,

求你快快答应我。

18求你前来拯救我,

把我从仇敌手中救赎出来。

19你知道我受的辱骂、欺凌和羞辱,

你看到了我仇敌的所作所为。

20他们的辱骂使我心碎,

令我绝望无助。

我渴望有人同情,却没有一个;

期望有人安慰,却无一人。

21他们给我苦胆当食物,

又拿醋给我解渴。

22愿他们面前的宴席变为网罗,

成为他们的陷阱。

23愿他们眼目昏暗,无法看见;

愿他们哆哆嗦嗦,直不起腰来。

24求你把烈怒倾倒在他们身上,

将怒气撒向他们。

25愿他们的家园一片荒凉,

愿他们的帐篷无人居住。

26因为他们迫害你击打过的人,

嘲笑你所打伤之人的痛苦。

27求你清算他们的种种罪行,

不要让他们有份于你的拯救之恩。

28愿他们的名字从生命册上被抹去,

不得和义人的名字列在一起。

29上帝啊,

我陷入痛苦和忧伤,

求你拯救我,保护我。

30我要用歌声赞美上帝的名,

以感恩的心尊崇祂。

31这要比献上有蹄有角的公牛等祭牲更讨耶和华喜悦。

32卑微的人看见这一切就欢喜快乐,

愿你们寻求上帝的人精神振奋。

33耶和华垂听穷苦人的祈求,

不轻看祂被囚的子民。

34愿天地都赞美祂,

愿海和其中的一切都赞美祂!

35因为上帝必拯救锡安

重建犹大的城邑。

祂的子民要住在那里,

拥有那片土地。

36祂仆人的后裔要承受那地方为业,

凡爱祂的人都要住在那里。