መዝሙር 68 NASV - 诗篇 68 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 68:1-35

መዝሙር 68

ብሔራዊ የድል መዝሙር

ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር፤ ማኅሌት

1እግዚአብሔር ይነሣ፤ ጠላቶቹ ይበተኑ፤

የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።

2ጢስ እንደሚበንን፣

እንዲሁ አብንናቸው።

ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣

ክፉዎችም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።

3ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤

በእግዚአብሔር ፊት ሐሤት ያድርጉ፤

ደስታንና ፍስሓን የተሞሉ ይሁኑ።

4ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም ተቀኙ፤

በደመናት ላይ የሚሄደውን ከፍ አድርጉት፤68፥4 ወይም በምድረ በዳ ለሚሄደው መንገድን አዘጋጁለት።

ስሙ እግዚአብሔር በተባለው ፊት፣

እጅግ ደስ ይበላችሁ።

5እግዚአብሔር በተቀደሰ ማደሪያው፣

ለድኻ አደጉ አባት፣ ለባልቴቲቱም ተሟጋች ነው።

6እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተ ሰብ መካከል ያኖራል፤68፥6 ወይም ብቸኞችን በገዛ ምድራቸው

እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃል፤

ዐመፀኞች ግን ምድረ በዳ ይኖራሉ።

7እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፣

በምድረ በዳም በተጓዝህ ጊዜ፣ ሴላ

8በሲና አምላክ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣

በእስራኤል አምላክ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣

ምድር ተንቀጠቀጠች፤

ሰማያትም ዶፍ አወረዱ።

9እግዚአብሔር ሆይ፣ በቂ ዝናብ አዘነብህ፤

ክው ብሎ የደረቀውን ርስትህን አረሰረስህ።

10መንጋህ መኖሪያው አደረጋት፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ ከበረከትህ ለድኾች ሰጠህ።

11ጌታ እንዲህ ሲል ቃሉን አስተላለፈ፤

ትእዛዙን የሚያውጁትም ብዙ ሰራዊት ናቸው፤

12“የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፤

በሰፈር የዋሉ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ።

13በበጎች በረት መካከል68፥13 ወይም በኮርቻ ማስቀመጫዎች ብትገኙ እንኳ፣

ከብር እንደ ተሠሩ የርግብ ክንፎች፣

በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ።”

14ሁሉን ቻዩ68፥14 ዕብራይስጡ ሻዳይ ይላል። በዚያ የነበሩትን ነገሥታት በበተነ ጊዜ፣

በሰልሞን እንደሚወርድ በረዶ አደረጋቸው።

15አንተ ብርቱ ተራራ፣ የባሳን ተራራ ሆይ፤

አንተ ባለ ብዙ ጫፍ ተራራ፣ የባሳን ተራራ፤

16እናንተ ባለ ብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፤

እግዚአብሔር ሊኖርበት የመረጠውን ተራራ፣

በእርግጥ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚኖርበትን ተራራ ለምን በምቀኝነት ዐይን ታያላችሁ?

17የእግዚአብሔር ሠረገላዎች እልፍ አእላፍ ናቸው፤

ሺህ ጊዜም ሺህ ናቸው፤

ጌታ ከሲና ወደ መቅደሱ ገባ።

18ወደ ላይ ዐረግህ፤

ምርኮ አጋበስህ፤

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ አንተ68፥18 ወይም እናንተ በዚያ ትኖር ዘንድ፣

ከዐመፀኞችም ሳይቀር፣

ከሰዎች ስጦታን ተቀበልህ።

19ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣

አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ። ሴላ

20አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤

ከሞት ማምለጥ የሚቻለውም በጌታ በእግዚአብሔር ነው።

21በእርግጥ እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፣

በኀጢአታቸውም የሚጸኑትን ሰዎች ጠጒራም አናት ይፈነካክታል።

22ጌታ እንዲህ ይላል፤ “ከባሳን መልሼ አመጣቸዋለሁ፤

ከባሕርም ጥልቀት አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤

23እግርህ በጠላትህ ደም ውስጥ እንዲጠልቅ፣

የውሻህም ምላስ ከጠላትህ ድርሻውን እንዲያገኝ ነው።”

24አምላክ ሆይ፤ የክብር አካሄድህ ታየ፤

ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያደርገው የክብር አካሄድ ነው።

25መዘምራን ከፊት፣ መሣሪያ የሚጫወቱ ከኋላ ሆነው ሲሄዱ፣

ከበሮ የሚመቱ ቈነጃጅትም በመካከላቸው ነበሩ።

26እግዚአብሔርን በጉባኤ አመስግኑት፤ ከእስራኤል ምንጭ የተገኛችሁ

እግዚአብሔርን አመስግኑ።

27የሚመራቸው ትንሹ ብንያም ነው፤

በዚያ በብዙ የሚቈጠሩ የይሁዳ መሳፍንት፣

እንዲሁም የዛብሎንና የንፍታሌም መሳፍንት ይገኛሉ።

28እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀይልህን እዘዝ፤68፥28 ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒምና የሱርስቱ ቅጅ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀይልህን ጥራ ይላሉ። አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን እግዚአብሔር ለአንተ ኀይል ይጠራልሃል ይላሉ።

አምላክ ሆይ ቀድሞ እንዳደረግህልን አሁንም ብርታትህን አሳየን።

29በኢየሩሳሌም ስላለው ቤተ መቅደስህ፣

ነገሥታት እጅ መንሻ ያመጡልሃል።

30በሸምበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣

በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኮርማ መንጋ ገሥጽ፤

ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤

ጦርነትን የሚወዱ ሕዝቦችንም በትናቸው።

31መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ፤

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

32የምድር መንግሥታት ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤

ለጌታ ተቀኙ። ሴላ

33ከጥንት ጀምሮ ከነበሩት ሰማያት በላይ ለወጣው፣

በኀያል ድምፁ ለሚያስገመግመው ዘምሩ።

34ግርማው በእስራኤል ላይ፣

ኀይሉም ከደመናት በላይ ነው፣

እግዚአብሔርን ብርታት የአንተ ነው በሉት።

35እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤

የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኀይልና ብርታትን ይሰጣል።

እግዚአብሔር ይባረክ!

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 68:1-35

第 68 篇

得胜的凯歌

大卫作的诗,交给乐长。

1愿上帝起来驱散祂的仇敌,

使恨祂的人四散奔逃。

2愿你驱散他们,

如风把烟吹散。

愿恶人在上帝面前灭亡,

如蜡在火中熔化。

3愿义人在上帝面前欢欣快乐,

愿他们高兴欢喜。

4要歌颂上帝,

赞美祂的名,

要颂扬驾云而行的上帝。

祂的名字是耶和华,

要在祂面前欢喜快乐。

5住在圣所的上帝是孤儿的父亲,寡妇的保护者。

6祂使孤苦者有家,

让被囚者欢然脱离牢笼。

但叛逆者要住在干旱之地。

7上帝啊,

你曾带领你的子民走过荒野。(细拉)

8那时,在西奈山的上帝面前,

以色列的上帝面前,

大地震动,诸天降雨。

9上帝啊,你降下沛雨,

滋润你干旱的产业——以色列

10让你的子民得以安居在那里。

上帝啊,

你满怀恩慈地供养穷苦人。

11主下达命令,

成群的妇女便奔走相告:

12“众王和他们的军队逃走了,逃走了!”

以色列的妇女都在分战利品。

13即使羊圈里的看羊人也披金戴银,

就像鸽子镀银的翅膀和金光闪闪的羽毛。

14全能的上帝驱散了众王,

势如大雪洒落在撒们

15巴珊的山巍峨雄壮,群峰耸立。

16崇山峻岭啊,

你们为何嫉妒地盯着上帝选为居所的山,

耶和华永远居住的地方呢?

17上帝带着千千万万的战车从西奈山来到祂的圣所。

18你升上高天时,

带着许多俘虏;

你接受了众人的礼物,

甚至叛逆者的礼物。

耶和华上帝就住在那里。

19要称颂主,

称颂我们的救主上帝,

祂天天背负我们的重担。(细拉)

20我们的上帝是拯救的上帝,

主耶和华救我们脱离死亡。

21上帝必打碎仇敌的头颅,

敲破怙恶不悛者的脑袋。

22主说:

“我要把他们从巴珊带回来,

从深海带回来,

23好让你们的脚从他们的血泊中踩过,

你们的狗也可以吃他们的肉。”

24上帝啊,你的队伍已经出现;

我的上帝,我的王啊,

你的队伍进了圣所,

25歌唱的在前,奏乐的殿后,

摇手鼓的少女居中。

26要在大会中赞美上帝,

以色列的会众都要赞美耶和华。

27最小的便雅悯支派在前领路,

后面跟着大群的犹大首领,

还有西布伦拿弗他利的首领。

28上帝啊,求你施展你的权能;

上帝啊,求你像以前一样为我们彰显你的力量。

29君王都带着礼物来到你耶路撒冷的圣殿。

30求你斥责那芦苇中的野兽,

斥责成群的公牛和列邦的牛犊,

使他们俯首献上贡银。

求你驱散好战的列邦。

31埃及的使节来朝见,

古实也要归降上帝。

32世上的列国啊,

要向上帝歌唱,

你们要歌颂主,

33歌颂凌驾在万古穹苍之上的主。

听啊,祂声如雷鸣。

34你们要传扬上帝的大能,

祂的威荣普照以色列

祂的权能彰显于穹苍。

35上帝啊,你在圣所中令人敬畏。

以色列的上帝把力量和权能赐给祂的子民。

上帝当受称颂!