መዝሙር 62 NASV - 诗篇 62 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 62:1-12

መዝሙር 62

ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ብቻ

ለመዘምራን አለቃ፤ ለኤዶታም፤ የዳዊት መዝሙር

1ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤

ድነቴም የሚመጣልኝ ከእርሱ ዘንድ ነው።

2ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤

መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።

3ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው?

ይህን የዘመመ ግድግዳ፣ የተንጋደደ ዐጥር፣

ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትሻላችሁ?

4ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣

ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤

ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤

በአፋቸው ይመርቃሉ፤

በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ

5ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤

ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ነውና።

6ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤

መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።

7መዳኔና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤62፥7 ወይም ልዑል እግዚአብሔር ድኅነቴና ክብሬ ነው ተብሎ መተርጐም ይችላል።

ብርቱ ዐለቴና መሸሸጊያዬ በእግዚአብሔር ነው።

8ሰዎች ሆይ፤ ሁል ጊዜ በእርሱ ታመኑ፤

ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤

እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ

9ከተናቀ ወገን መወለድ ከንቱ፣

ከከበረውም መወለዱ ሐሰት ነው።

በሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም፣

ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው።

10በዝርፊያ አትታመኑ፤

በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤

በዚህ ብትበለጽጉም፣

ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።

11እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤

እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤

ኀይል የእግዚአብሔር ነው።

12ጌታ ሆይ፤ ምሕረትም የአንተ ነው፤

አንተ ለእያንዳንዱ፣

እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 62:1-12

第 62 篇

唯上帝是拯救

大卫作的训诲诗,交给乐长,照耶杜顿的做法。

1我的心默默等候上帝,

祂是我的拯救者。

2唯有祂才是我的磐石,

我的拯救,我的堡垒,

我必不致动摇。

3我就像一面摇摇欲坠的墙壁、行将倒塌的篱笆,

你们要攻击我、置我于死地到何时呢?

4你们千方百计把我从高位拉下。

你们善于说谎,嘴上祝福,

心却咒诅。(细拉)

5我的心啊!要默默等候上帝,

因为我的盼望从祂而来。

6唯有祂才是我的磐石,

我的拯救,我的堡垒,

我必不致动摇。

7上帝是我的拯救者,

是我的荣耀,

祂是我的坚固磐石,

是我的避难所。

8众百姓啊,

要时刻信靠上帝,

向祂倾心吐意,

因为祂是我们的避难所。(细拉)

9卑贱人不过是一丝气息,

尊贵人不过是一场幻影,

把他们放在天平上一秤,

比空气还轻,毫无分量。

10不要敲诈勒索,

不要妄想靠偷盗发财,

即使财富增多,也不要倚靠它。

11上帝再三告诉我:

祂拥有权能,

12充满慈爱。

主啊,你必照各人的行为来施行赏罚。