መዝሙር 6 NASV - 诗篇 6 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 6:1-10

መዝሙር 6

በጭንቅ ጊዜ የቀረበ ጸሎት

ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር በሸሚኒት6፥0 የ6 መግቢያ ርእስ ሲሆን በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ

አትገሥጸኝ፤

በመዓትህም አትቅጣኝ።

2እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ።

3ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤

እስከ መቼ፤ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል?

4እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤

ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤

5በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤

በሲኦልስ6፥5 ወይም በመቃብር ማን ያመሰግንሃል?

6ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ፤

ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤

መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።

7ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤

ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኖአቸዋል።

8እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤

እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቶአልና።

9እግዚአብሔር ልመናዬን አድምጦአል፤

እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል።

10ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ እጅግም ይደነግጣሉ፤

በመጡበት ይመለሳሉ፤ ድንገትም ይዋረዳሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 6:1-10

第 6 篇

患难中祈求怜悯

大卫的诗,交给乐长,弦乐器伴奏。

1耶和华啊,

求你不要在怒中责备我,

不要在烈怒中惩罚我。

2耶和华啊,求你怜悯,

因为我软弱无力。

耶和华啊,求你医治,

因为我痛彻入骨。

3我心中忧伤,

耶和华啊,

你要我忧伤到何时呢?

4耶和华啊,求你回来救我,

因你的慈爱而拯救我。

5因为死去的人不会记得你,

谁会在阴间赞美你呢?

6我因哀叹心力交瘁,

夜夜哭泣,泪漂床榻,

湿透被褥。

7我的眼睛因忧愁而模糊,

因敌人的攻击而昏花。

8你们所有作恶的人,快走开!

因为耶和华已经听见我的哭声。

9耶和华听见了我的恳求,

祂必答应我的祷告。

10我所有的仇敌都必羞愧,

惊恐不已;

他们必忽然蒙羞,

掉头逃窜。