መዝሙር 58 NASV - 诗篇 58 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 58:1-11

መዝሙር 58

የምድር ዳኞች ፈራጅ

ለመዘምራን አለቃ፤ “አታጥፋ” በሚለው ቅኝት የሚዘመር፤ የዳዊት ቅኔ58፥0 ርእሱ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1ኀያላን ሆይ፤ በውኑ ጽድቅ ከአፋችሁ ይወጣል?

የሰው ልጆች ሆይ፤ በቅን ትፈርዳላችሁን?

2የለም፤ በልባችሁ ክፋትን ታውጠነጥናላችሁ፤

በእጃችሁም ዐመፅን በምድር ላይ ትጐነጒናላችሁ።

3ክፉዎች በማሕፀን ሳሉ ከመንገድ የወጡ ናቸው፤

ሲወለዱ ጀምሮ የተሳሳቱና ውሸታሞች ናቸው።

4መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤

አልሰማ ብላ ጆሮዋን እንደ ደፈነች እፉኝት ናቸው፤

5ጆሮዋንም የደፈነችው የመተተኛውን

ወይም የጠቢቡን ደጋሚ ቃል ላለመስማት ነው።

6አምላክ ሆይ፤ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንበሶቹን መንጋጋ አወላልቅ!

7ፈጥኖ እንደሚያልፍ ወራጅ ውሃ ይጥፉ፤

ቀስታቸውን ሲስቡ ፍላጻቸው ዱልዱም ይሁን።

8ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤

ፀሓይን እንደማያይ ጭንጋፍ ይሁኑ።

9የእሾኽ እሳት ገና ድስታችሁን ሳያሰማው፣

እርጥቡንም ደረቁንም እኩል በዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።58፥9 በዕብራይስጡ የዚህ ሐረግ ትርጒም በትክክል አይታወቅም።

10ጻድቃን በቀልን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል፤

እግራቸውንም በግፈኞች ደም ይታጠባሉ።

11ሰዎችም፣ “በእርግጥ ለጻድቃን ብድራት ተቀምጦላቸዋል፤

በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 58:1-11

第 58 篇

祈求上帝惩罚恶人

大卫作的诗,交给乐长,调用“休要毁坏”。

1你们做官长的主持公道吗?

你们的审判公正吗?

2不,你们心中图谋不义,

你们在地上行凶作恶。

3恶人生下来就步入歧途,

一出母胎就离开正道,

谎话连篇。

4他们像喷出毒液的毒蛇,

又像耳聋的眼镜蛇,

5任法师的邪术再高超,

也听不见他的咒语。

6上帝啊,求你敲碎他们的牙齿;

耶和华啊,

求你拔掉这些猛狮的利齿。

7愿他们如流水逝去,

愿他们弯弓搭箭时箭头折断。

8愿他们像蜗牛一样溶为烂泥,

又如流产的胎儿不见天日。

9刹那间,

荆棘还没有把锅烧热的工夫,

上帝必除灭他们。

10义人必因恶人遭报而欢欣,

并用恶人的血洗脚。

11这样,人们必说:

“义人终有善报,

确实有一位审判天下的上帝。”