መዝሙር 56 NASV - 诗篇 56 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 56:1-13

መዝሙር 56

በእግዚአብሔር መደገፍ

ለመዘምራን አለቃ፤ “ርግቢቱ ሩቅ ባለው ወርካ ላይ” በተባለው ቅኝት፤ ፍልስጤማውያን በጌት በያዙት ጊዜ፤ የዳዊት ቅኔ56፥0 ርእሱ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤

ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል።

2ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤

በትዕቢት የሚዋጉኝ ብዙዎች ናቸውና።

3ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣

እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።

4ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣

በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤

ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

5ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤

ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ።

6ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤

ርምጃዬን ይከታተላሉ፤

ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ።

7እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቶ እንዳያመልጡ፣

ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።

8ሰቆቃዬን መዝግብ፤

እንባዬን በዕቃህ አጠራቅም፤56፥8 እንባዬን በወይን አቍማዳህ ውስጥ ጨምር ወይም እንባዬን በመጽሐፍህ መዝገብ

ሁሉስ በመዝገብህ የተያዘ አይደለምን?

9ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣

ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤

በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።

10ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣

ቃሉን በማመሰግነው በእግዚአብሔር

11በአምላክ ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤

ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

12እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተ ስእለት አለብኝ፤

የማቀርብልህም የምስጋና መሥዋዕት ነው፤

13በሕያዋን ብርሃን፣56፥13 ወይም እኔን ከሞት

በእግዚአብሔር ፊት እመላለስ ዘንድ፣

ነፍሴን ከሞት፣56፥13 ወይም በሕያዋን ምድር

እግሬንም ከመሰናክል አድነሃልና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 56:1-13

第 56 篇

信靠上帝的祷告

大卫作的诗,交给乐长,调用“远方无声鸽”,大卫在迦特被非利士人抓住时所作。

1上帝啊,求你怜悯我,

因为仇敌攻击我,整日迫害我。

2我的仇敌整日攻击我,

许多人狂妄地迫害我。

3我害怕的时候,

仍要倚靠你。

4我赞美上帝的应许,

我信靠祂,就不惧怕,

区区世人能把我怎样?

5他们整天歪曲我的话,

总是图谋害我。

6他们勾结起来,

暗中监视我的行踪,

伺机害我。

7上帝啊,

不要让这些作恶的人逃脱,

求你在怒中毁灭他们。

8你知道我的哀伤,

你把我的眼泪收在袋中。

我的遭遇都记录在你的册子上。

9我向你求救的时候,

敌人都落荒而逃。

我知道上帝是我的帮助。

10我因上帝的应许而赞美祂,

我因耶和华的应许而赞美祂。

11我信靠上帝,就不惧怕,

区区世人能把我怎样?

12上帝啊,

我要恪守向你发的誓言,

献上感恩祭。

13因为你救我脱离死亡,

使我没有跌倒,

让我可以活在你面前,

沐浴生命之光。