መዝሙር 54 NASV - 诗篇 54 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 54:1-7

መዝሙር 54

ለፍትሕ አምላክ የቀረበ አቤቱታ

ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች፤ ዜፋውያን ወደ ሳኦል መጥተው፣ “ዳዊት በእኛ ዘንድ ተደብቆአል” ባሉት ጊዜ፤ የዳዊት ትምህርት።54፥0 ርእሱ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ አድነኝ፤

በኀይልህም ፍረድልኝ።

2እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤

የአፌንም ቃል አድምጥ።

3ባዕዳን ተነሥተውብኛልና፤

ግፈኞች ነፍሴን ሽተዋታል፤

እግዚአብሔርንም ከምንም አልቈጠሩም። ሴላ

4እነሆ፤ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፤

ጌታም ደግፎ ይይዘኛል።

5የገዛ ክፋታቸው በሚያደቡብኝ ላይ ይመለስባቸው፤

በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው።

6በበጎ ፈቃድ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ነውና፣

ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤

7ከመከራ ሁሉ ታድጎኛልና፤

ዐይኔም የጠላቶቼን ውድቀት ለማየት በቅቶአል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 54:1-7

第 54 篇

祈求上帝的拯救

西弗人去告诉扫罗:“大卫藏在我们那里”,那时大卫作了这首训诲诗,交给乐长,用弦乐器。

1上帝啊,

求你凭你的名拯救我!

求你用你的大能为我申冤!

2上帝啊,求你垂听我的祷告,

留心我口中的话。

3因为傲慢的人起来攻击我,

目无上帝的暴徒正寻索我的性命。(细拉)

4看啊,上帝帮助我,主扶持我,

5祂必使我的仇敌自作自受。

信实的上帝啊,

求你毁灭他们。

6耶和华啊,

我甘心乐意献上祭物,

我要赞美你的名,

因为你的名是美善的。

7你拯救我脱离一切艰难,

让我傲视仇敌。