መዝሙር 53 NASV - 诗篇 53 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 53:1-6

መዝሙር 53

አምላክ የለሾች

53፥1-6 ተጓ ምብ – መዝ 14፥1-7

ለመዘምራን አለቃ፤ በማኸላት፤ የዳዊት ትምህርት።53፥0 ርእሱ ምናልባት የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1ቂል በልቡ፣

“እግዚአብሔር የለም” ይላል።

ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤

በጎ ነገርን የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም።

2በማስተዋል የሚመላለስ፣

እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣

እግዚአብሔር ከሰማይ፣

ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።

3ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤

በአንድነትም ተበላሹ፤

አንድ እንኳ፣

በጎ የሚያደርግ የለም።

4ሰው እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉት፣

እግዚአብሔርንም ጠርተው የማያውቁት፣

እነዚያ ክፉ አድራጊዎች ከቶ አይማሩምን?

5የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣

በዚያ፣ በፍርሀት ተዋጡ፤

እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤

እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው።

6ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በወጣ!

እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣

ያዕቆብ ሐሤት ያድርግ፤ እስራኤል ደስ ይበለው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 53:1-6

第 53 篇

人的邪恶

大卫作的训诲诗,交给乐长,调用“麻哈拉”。

1愚昧人心里想:

“没有上帝。”

他们全然败坏,行为邪恶,

无人行善。

2上帝从天上俯视人间,

要看世上有没有明智者,

有没有寻求祂的人。

3人们都背弃祂,

都败坏不堪,无人行善,

连一个都没有!

4恶人吞吃我的百姓如同吃饭,

他们不求告上帝。

难道他们无知吗?

5因此,他们必陷入空前的惊恐。

上帝必使攻击你的仇敌粉身碎骨,

你必使他们蒙羞受辱,

因为上帝弃绝了他们。

6以色列的拯救来自锡安

上帝救回祂被掳的子民时,

雅各要欢喜,以色列要快乐。