መዝሙር 52 NASV - 诗篇 52 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 52:1-9

መዝሙር 52

የክፉዎች ዕጣ ፈንታ

ለመዘምራን አለቃ፤ ኤዶማዊው ዶይቅ ወደ ሳኦል መጥቶ፣ “ዳዊት ወደ አቢሜሌክ ቤት መጥቶአል” ብሎ በነገረው ጊዜ፤ የዳዊት52፥0 ርእሱ ምናልባት የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። ትምህርት

1ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ?

አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣

እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ?

2አንተ ማታለልን ሥራዬ ብለህ የያዝህ፤

አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ፣

ጥፋትን ያውጠነጥናል።

3ከበጎ ነገር ይልቅ ክፋትን፣

እውነትን ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ወደድህ። ሴላ

4አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፤

ጐጂ ቃላትን ሁሉ ወደድህ!

5እግዚአብሔር ግን ለዘላለም

ያንኰታኵትሃል፤

ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤

ከሕያዋንም ምድር ይነቅልሃል። ሴላ

6ጻድቃን ይህን ዐይተው ይፈራሉ፤

እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤

7“እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣

ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ፣

በክፋቱም የበረታ፣

ያ ሰው እነሆ!”

8እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት፣

እንደለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤

ከዘላለም እስከ ዘላለም፣

በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ።

9ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤

ስምህ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤

በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 52:1-9

第 52 篇

上帝的审判和慈爱

以东人多益去告诉扫罗:“大卫到了亚希米勒家。”那时大卫作了这首训诲诗,交给乐长。

1勇士啊,你为何以作恶为荣?

上帝的慈爱永远长存。

2你这诡诈的人啊,

舌头利如剃刀,

尽是害人的奸计。

3你喜爱邪恶,不爱良善;

你喜爱虚谎,不爱真理。(细拉)

4你有诡诈的舌头,

好说恶言恶语。

5上帝必永远毁灭你,

祂必抓住你,

把你从家里拉出来,

从活人之地铲除。(细拉)

6义人看见必心生敬畏,

他们必嘲笑说:

7“看啊,这就是不依靠上帝的人,

他只倚仗自己的财富和以残暴手段获得的权势。”

8我就像上帝殿中的一棵橄榄树,枝繁叶茂,

我永永远远信靠上帝的慈爱。

9上帝啊,

我要永远赞美你的作为。

我要在你忠心的子民面前仰望你美善的名。