መዝሙር 49 NASV - 诗篇 49 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 49:1-20

መዝሙር 49

የሀብት ከንቱነት

ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር።

1እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤

በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ።

2ዝቅተኞችና ከፍተኞች፤

ባለጠጎችና ድኾች ይህን በአንድነት ስሙ።

3አፌ የጥበብን ቃል ይናገራል፤

የልቤም ሐሳብ ማስተዋልን ይሰጣል።

4ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤

እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።

5የአጭበርባሪዎች ክፋት በከበበኝ ጊዜ፣

በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?

6በሀብታቸው የሚመኩትን፣

በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ?

7የሌላውን ሕይወት መቤዠት የሚችል ሰው፣

ወይም ለእግዚአብሔር ወጆ የሚከፍልለት ማንም የለም።

8የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና፤

በቂ ዋጋም ከቶ ሊገኝለት አይችልም፤

9በዚህም ዘላለም ይኖራል፣

መበስበስንም አያይም።

10ጠቢባን ሟች መሆናቸው የሚታይ ነው፤

ቂልና ሞኝም በአንድነት ይጠፋሉ፤

ጥሪታቸውንም ለሌላው ጥለው ይሄዳሉ።

11መሬቶችን በስማቸው ቢሰይሙም፣

መቃብራቸው የዘላለም ቤታቸው፣

ከትውልድ እስከ ትውልድም መኖሪያቸው ይሆናል።

12ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤

ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።49፥12 በሰብዓ ሊቃናት ትርጒምና በሱርስቱ ቅጂ ቍ 12 ከቍ 20 ጋር አንድ ዐይነት ነው፤ ዕብራይስጡ ግን ከዚህ ይለያል።

13ይህ የተላላዎች ዕድል ፈንታ፣

የእነርሱንም አባባል ተቀብለው ለሚከተሏቸው፣

መጨረሻ ግብ ነው። ሴላ

14እንደ በጎች ለሲኦል49፥14 በዚህ እና በቍ 15 ላይ ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል አንዳንድ የእንግሊዝኛ ቅጆች ግን መቃብር ይላሉ። የተዳረጉ ናቸው፤

ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤

ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤

አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣

በሲኦል ይፈራርሳል።

15እግዚአብሔር ግን ነፍሴን49፥15 ወይም ሕይወቴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል፤

በርግጥም በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለኝ። ሴላ

16ሰው ባለጠጋ ሲሆን፣

የቤቱም ክብር ሲበዛለት አትፍራ፤

17በሚሞትበትም ጊዜ ይዞት የሚሄደው አንዳች የለምና፤

ክብሩም አብሮት አይወርድም።

18በሕይወት ሳለ ራሱን እንደ ተባረከ ቢቈጥርም፣

ሰዎች በበለጸግህ ጊዜ ቢያወድሱህም፣

19ብርሃን ከቶ ወደማያዩት፣

ወደ አባቶች ማኅበር ይቀላቀላል።

20ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤

ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 49:1-20

第 49 篇

财富的虚幻

可拉后裔的诗,交给乐长。

1万民啊,你们要听!

世人啊,

2不论贵贱贫富,都要留心听!

3因为我口出智慧,心思明智。

4我要侧耳听箴言,

弹琴解释人生之谜。

5危难来临,四面被奸诈之徒包围时,我何必惧怕?

6他们倚靠金钱、夸耀财富,

7却不能救赎自己的生命,

也无法向上帝付生命的赎价。

8因为生命的赎价高昂,

无人付得起,

9以致可以永远活着,不进坟墓。

10众所周知,即使智者也要死去,

愚人和庸者也要灭亡,

将他们的财富留给别人。

11尽管他们用自己的名字来为产业命名,

坟墓却是他们永远的归宿,

世代的住处。

12人不能长享富贵,

终必死去,与兽无异。

13这就是愚昧人及其追随者的下场!(细拉)

14他们注定要死,与羊无异,

死亡是他们的牧者;

到了早晨,

他们必被正直人管辖。

他们的躯体必朽烂在坟墓里,

远离自己的豪宅。

15但上帝必救赎我的生命脱离死亡的权势,

接我到祂身边。(细拉)

16因此,见他人财富增多,

日益奢华,

不要害怕。

17因为他们死后什么也带不走,

再不能拥有荣华富贵。

18他们活着时自以为有福,

人们都赞扬他们的成就,

19到头来他们还是要归到祖先那里,

再也看不见光明。

20人有财富,却无明智的心,

无异于必死的兽类。