መዝሙር 45 NASV - 诗篇 45 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 45:1-17

መዝሙር 45

የንጉሣዊ ሰርግ መዝሙር

ለመዘምራን አለቃ፤ “በጽጌረዳ” ዜማ፤ የቆሬ ልጆች ትምህርት፤ የፍቅር መዝሙር45፥0 የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1ልቤ መልካም ሐሳብ አፈለቀ፤

የተቀኘሁትን ቅኔ ለንጉሥ አሰማለሁ፤

አንደበቴም እንደ ባለ ሙያ ጸሓፊ ብርዕ ነው።

2አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ፤

ከንፈሮችህም የጸጋ ቃል ያፈልቃሉ፤

ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል።

3ኀያል ሆይ፤ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ፤

ግርማ ሞገስንም ተላበስ።

4ስለ እውነት፣ ስለ ትሕትና ስለ ጽድቅ፣

ሞገስን ተጐናጽፈህ በድል አድራጊነት ገሥግሥ፤

ቀኝ እጅህም ድንቅ ተግባር ታሳይ።

5የሾሉ ፍላጻዎችህ በንጉሥ ጠላቶች ልብ ይሰካሉ፤

ሕዝቦችም ከእግርህ በታች ይወድቃሉ።

6አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይኖራል፤

የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ናት።

7ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤

ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣

ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።

8ልብስህ ሁሉ በከርቤ፣ በአደስና በጥንጁት መዐዛ ያውዳል፤

በዝኆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶችም፣

የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኙሃል።

9ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤

ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።

10ልጄ ሆይ፤ አድምጪ፤ አስተዉይ፤ ጆሮሽንም አዘንብይ፤

ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።

11ንጉሥ በውበትሽ ተማርኮአል፤

ጌታሽ ነውና አክብሪው።

12የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤45፥12 ወይም፣ የጢሮሳውያን ልብስ ተክህኖ ከስጦታዎቹ መካከል አለ

ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።

13የንጉሥ ልጅ ከላይ እስከ ታች ተሸልማ እልፍኟ ውስጥ አለች፤

ልብሷም ወርቀ ዘቦ ነው።

14በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሥ ትወሰዳለች፤

ደናግል ጓደኞቿም ተከትለዋት፣

ወደ አንተ ይመጣሉ።

15በደስታና በሐሤት ወደ ውስጥ ይመሯቸዋል፤

ወደ ንጉሡም ቤተ መንግሥት ይገባሉ።

16ወንዶች ልጆችህ በአባቶችህ እግር ይተካሉ፤

ገዦችም አድርገሽ በምድር ሁሉ ትሾሚያቸዋለሽ።

17ስምሽን በትውልድ ሁሉ ዘንድ መታሰቢያ አደርጋለሁ፤

ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ያወድሱሃል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 45:1-17

第 45 篇

婚礼诗歌

可拉后裔作的训诲诗,也是婚礼上唱的情歌,交给乐长,调用“百合花”。

1我心中涌出美丽的诗章,

我要把它献给王,

我的舌头是诗人手上的妙笔。

2你俊美无比,口出恩言,

因此上帝永远赐福给你。

3伟大的王啊,

佩上你的宝剑,

你是何等尊贵、威严!

4你威严无比,所向披靡,

捍卫真理和正义,

保护卑微的人。

愿你的右手彰显可畏的作为!

5你的利箭刺穿敌人的心窝,

列国臣服在你脚下。

6上帝啊,你的宝座永远长存,

你以公义的杖执掌王权。

7你喜爱公义,憎恶邪恶,

因此上帝,你的上帝,

用喜乐之油膏你,

使你超过同伴。

8你的衣袍散发出没药、沉香和肉桂的芬芳,

你陶醉在象牙宫的弦乐中。

9众公主在你的贵客中,

俄斐金饰的王后站在你右边。

10女子啊,

要侧耳倾听:不要再挂念家乡的父老,

11王喜欢你的美貌,

你要敬重他,因他是你的主。

12泰尔人必来送礼,

富人必来取悦你。

13公主身穿金线衣,无比华贵。

14她身披锦绣,

由侍女伴随前来见王,

15她们欢喜快乐地进入王宫。

16你的子孙将来要继承祖先的王位,

你要立他们在各地做王。

17我要使你的名世代受尊崇,

万民必永远称谢你。