መዝሙር 44 NASV - 诗篇 44 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 44:1-26

መዝሙር 44

ብሔራዊ ሰቆቃ

ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች ትምህርት።44፥0 የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1አምላክ ሆይ፤ በጆሮአችን ሰምተናል፤

አባቶቻችን በቀድሞ ዘመን፣

እነርሱ በነበሩበት ዘመን፣

ያደረግኸውን ነግረውናል።

2ሕዝቦችን በእጅህ አሳደህ አወጣሃቸው፤

አባቶቻችንን ግን ተከልሃቸው፤

ሕዝቦችን አደቀቅህ፤

አባቶቻችንን ግን ነጻ አወጣሃቸው።

3ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤

ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤

አንተ ወደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣

ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።

4እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ንጉሤ ነህ፤44፥4 የሰብዓ ሊቃናት ትርጒም የሱርስቱ ቅጅ ንጉሤ ነህ፤ አምላኬም ነህ ይላሉ፤ ዕብራይስጡ ደግሞ፣ ንጉሤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይላል።

ያዕቆብም ድል እንዲያደርግ የወሰንህ አንተ ነህ።

5በአንተ ጠላቶቻችን በመጡበት እንዲመለሱ እናደርጋለን፤

በስምህም ባላጋራዎቻችንን ከእግራችን በታች እንረግጣለን።

6በቀስቴ አልተማመንም፤

ሰይፌም አያስጥለኝም።

7አንተ ግን በጠላቶቻችን ላይ ድልን ትሰጠናለህ፤

ባላንጣዎቻችንንም ታሳፍራለህ።

8ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤

ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን። ሴላ

9አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤

ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም።

10ከጠላት ፊት እንድናፈገፍግ አደረግኸን፤

ባላንጣዎቻችንም ዘረፉን።

11እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤

በሕዝቦችም መካከል በተንኸን።

12ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤

ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም።

13ለጎረቤቶቻችን ስድብ፣

በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።

14በሕዝቦች ዘንድ መተረቻ፣

በሰዎች መካከል በንቀት ራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።

15ውርደቴ ቀኑን ሙሉ በፊቴ ነው፤

ፊቴም ዕፍረትን ተከናንቦአል።

16ይህም ከሚዘልፍና ከሚያላግጥ ሰው ድምፅ የተነሣ፣

ከጠላትና ከተበቃይ ሁኔታ የተነሣ ነው።

17አንተን ሳንረሳ፣

ለኪዳንህም ታማኝነታችንን ሳናጓድል፣

ይህ ሁሉ ደረሰብን።

18ልባችን ወደ ኋላ አላለም፤

እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።

19አንተ ግን ተኵላዎች በሚውሉበት ቦታ ሰባብረህ ጣልኸን፤

በሞት ጥላም ሸፈንኸን።

20የአምላካችንን ስም ረስተን፣

እጃችንንም ወደ ባዕድ አምላክ ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣

21እግዚአብሔር ይህን ማወቅ ይሳነዋልን?

እርሱ ልብ የሰወረውን የሚረዳ ነውና።

22ይሁን እንጂ ቀኑን ሙሉ ስለ አንተ ሞትን እንጋፈጣለን፤

እንደሚታረዱ በጎችም ተቈጥረናል።

23ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ?

ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።

24ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?

መከራችንንና መጠቃታችንን ለምን ትረሳለህ?

25ነፍሳችን ዐፈር ውስጥ ሰጥማለች፤

ሆዳችንም ከምድር ጋር ተጣብቆአል።

26ተነሥና እርዳን!

ስለ ምሕረትህ ስትል ተቤዠን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 44:1-26

第 44 篇

祈求上帝保护

可拉后裔作的训诲诗,交给乐长。

1上帝啊,

我们亲耳听过祖先讲述你在古时,

在我们祖先时代的作为。

2你亲手赶出外族,

把我们的祖先安置在那里;

你击溃列邦,

使我们的祖先兴旺发达。

3他们不是靠自己的刀剑征服那里,

不是靠自己的臂膀得胜,

而是靠你的权能、力量和恩惠,

因为你爱他们。

4你是我的君王,我的上帝;

你让雅各得胜。

5我们靠你击退敌人,

靠你的名践踏仇敌。

6我不倚靠我的弓,

我的剑不能使我得胜。

7只有你使我们战胜敌人,

使我们的仇敌蒙羞。

8上帝啊,我们终日以你为荣,

我们永远赞美你。(细拉)

9现在你却丢弃我们,

让我们受辱,

不再帮我们的军队作战。

10你使我们在仇敌面前败退,

遭敌人掳掠。

11你使我们如被宰杀的羊,

将我们分散在列国。

12你把我们廉价卖掉,

视我们一文不值。

13你使我们遭四邻辱骂,

被周围人讥讽、嘲笑。

14你使我们成为列国的笑柄,

人们对我们连连摇头。

15我终日受辱,满面羞愧,

16因为咒骂和毁谤我的人讥笑我,仇敌报复我。

17虽然这一切临到我们身上,

我们却没有忘记你,

也没有违背你的约。

18我们对你没有异心,

也没有偏离你的道路。

19你在豺狼出没的地方压碎我们,

使死亡的阴影笼罩我们。

20倘若我们忘记我们的上帝,

或举手向外邦的神明祷告,

21上帝怎会不知道呢?

祂洞悉人心中的秘密。

22为了你,我们终日出生入死,

被视为待宰的羊。

23主啊,求你醒来,

你为何沉睡?

求你起来,不要永远丢弃我们。

24你为何掩面不理我们,

不理会我们所受的苦难和压迫?

25我们扑倒在地,横卧在尘土中。

26求你起来帮助我们,

施慈爱救赎我们。