መዝሙር 43 NASV - 詩篇 43 CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 43:1-5

መዝሙር 4343፥0 በብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች መዝሙር 42 እና 43 አንድ መዝሙር ነው።

በስደት ላይ ያለ ሌዋዊ ልቅሶ

1አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤

ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፤

ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።

2አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣

ለምን ተውኸኝ?

ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣

ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?

3ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤

እነርሱ ይምሩኝ፤

ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣

ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ።

4እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤

ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣

በበገና አመሰግንሃለሁ።

5ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?

ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?

ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤

አዳኜና አምላኬን፣

ገና አመሰግነዋለሁና።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 43:1-5

第 43 篇

流亡異鄉者的禱告

1上帝啊,

求你為我伸張正義,

在不虔敬的人面前為我辯護,

救我脫離詭詐邪惡的人。

2你是保護我的上帝,

你為何丟棄我?

為何讓我受仇敵的攻擊,

使我哀傷不已呢?

3求你以光明和真理引導我,

領我到你的聖山,到你的居所。

4我要到上帝的祭壇前,

到賜我喜樂的上帝面前。

上帝啊,我的上帝,

我要彈琴讚美你。

5我的心啊!

你為何沮喪?為何煩躁?

要仰望上帝,

因為我還要讚美祂——我的救主,我的上帝。