መዝሙር 42 NASV - 诗篇 42 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 42:1-11

ሁለተኛ መጽሐፍ

ከመዝሙር 42–72

መዝሙር 42

42፥0 በብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች መዝሙር 42 እና 43 አንድ መዝሙር ነው።

በስደት ላይ ያለ ሌዋዊ ልቅሶ

1ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣

አምላክ ሆይ፤ ነፍሴም እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች።

2ነፍሴ አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማች፤

መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው?

3ሰዎች ቀኑን ሙሉ፣

“አምላክህ የት አለ?” ባሉኝ ቍጥር፣

እንባዬ ቀንና ሌሊት፣

ምግብ ሆነኝ።

4ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች፣

እነዚህን ነገሮች አስታወስሁኝ፤

ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ፣

በእልልታና በምስጋና መዝሙር፣

በአእላፍ ሕዝብ መካከል፣

እንዴት ከሕዝቡ ጋር እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ።

5ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?

ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?

ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤

አዳኜና 6አምላኬን፣ ገና አመሰግነዋለሁና።

ነፍሴ በውስጤ ተክዛለች፤

ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር፣

በአርሞንኤም ከፍታ፣ በሚዛር ተራራ አስብሃለሁ።

7በፏፏቴህ ማስገምገም፣

አንዱ ጥልቅ ሌላውን ጥልቅ ይጣራል፤

ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣

ሙሉ በሙሉ አጥለቀለቀኝ።

8እግዚአብሔር ምሕረቱን በቀን ያዝዛል፤

ዝማሬውም በሌሊት በእኔ ዘንድ አለ፤

ይህም ለሕይወቴ አምላክ የማቀርበው ጸሎት ነው።

9እግዚአብሔር ዐለቴን፣

“ለምን ረሳኸኝ?

ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣

ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?” እለዋለሁ።

10ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣

“አምላክህ የት አለ?” እያሉ፣

በነገር ጠዘጠዙኝ፣

ዐጥንቴም ደቀቀ።

11ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?

ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?

ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፣

አዳኜና አምላኬን፣

ገና አመሰግነዋለሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 42:1-11

卷二:诗篇42—72

第 42 篇

流落异乡者的祷告

可拉后裔作的训诲诗,交给乐长。

1上帝啊,我的心切慕你,

像鹿切慕溪水。

2我心里渴慕上帝,

渴慕永活的上帝,

我何时才能去朝拜祂呢?

3我不吃不喝,昼夜以泪洗面,

人们整天讥笑我:

“你的上帝在哪里?”

4从前我带领众人浩浩荡荡去上帝的殿,

在欢呼、感恩声中一起过节。

我回想这些事,

心中无限忧伤。

5我的心啊!

你为何沮丧?为何烦躁?

要仰望上帝,

因为我还要赞美祂——我的救主,我的上帝。

6我的上帝啊,我心中沮丧,

便在约旦河、黑门山和米萨山想起你。

7你的瀑布发出巨响,

回荡在深渊之间,

你的洪涛巨浪淹没我。

8白天耶和华将祂的慈爱浇灌我;

夜间我歌颂祂,

向赐我生命的上帝祷告。

9我对上帝——我的磐石说:

“你为何忘记我?

为何要我受仇敌的攻击,使我哀伤不已呢?”

10仇敌的辱骂刺骨钻心。

他们整天对我说:

“你的上帝在哪里?”

11我的心啊!

你为何沮丧?为何烦躁?

要仰望上帝,

因为我还要赞美祂——我的救主,我的上帝。