መዝሙር 4 NASV - 诗篇 4 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 4:1-8

መዝሙር 4

የሠርክ ጸሎት

ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዜም የዳዊት መዝሙር

1የጽድቄ አምላክ ሆይ፤

በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤

ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤

ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።

2ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅ4፥2 ወይም ወደ ራሳችሁ ታደርጋላችሁ?

እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? ሐሰትንስ4፥2 ወይም የሐሰት አማልክት ትሻላችሁ? ሴላ

3እግዚአብሔር ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፤

እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።

4ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤

በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣

ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ

5የጽድቅን መሥዋዕት አቅርቡ፤

በእግዚአብሔርም ታመኑ።

6ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል? ይላሉ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።

7ስንዴና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ባመረቱ ጊዜ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ፣

አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል።

8በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 4:1-8

第 4 篇

求助的晚祷

大卫的诗,交给乐长,弦乐器伴奏。

1称我为义人的上帝啊!

我呼求的时候,求你回答。

你曾救我脱离困境,

现在求你怜悯我,

垂听我的祷告。

2世人啊!你们把我的荣耀变为羞辱要到何时呢?

你们追求虚谎之事要到何时呢?(细拉)

3要知道,耶和华已经把敬虔人分别出来,使之圣洁,归祂自己。

祂必垂听我的祈求。

4不要因生气而犯罪;

躺在床上的时候要默然思想。(细拉)

5要献上当献的祭物,

信靠耶和华。

6许多人说:“谁会善待我们呢?”

耶和华啊,

求你的圣容光照我们。

7你使我比那收获五谷新酒的人更喜乐。

8只有你耶和华使我安然居住,

我必高枕无忧。