መዝሙር 39 NASV - 诗篇 39 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 39:1-13

መዝሙር 39

ታላቅ እግዚአብሔር - ታናሽ ሰው

ለመዘምራን አለቃ፣ ለኤዶታም፤ የዳዊት መዝሙር

1እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣

መንገዴን እጠብቃለሁ፤

ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣

ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ።

2እንደ ዲዳ ዝም አልሁ፤

ለበጎ ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤

ሆኖም ጭንቀቴ ባሰ።

3ልቤ በውስጤ ጋለ፤

በማሰላስልበትም ጊዜ እሳቱ ነደደ፤

ከዚያም በአንደበቴ እንዲህ ተናገርሁ፤

4እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣

የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤

አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።

5እነሆ፤ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አስቀመጥህ፤

ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፤

በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ተን ነው። ሴላ

6ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤

በከንቱም ይታወካል፤

ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል።

7“ጌታ ሆይ፤ አሁንስ ወደ ማን ልመልከት?

ተስፋዬ በአንተ ላይ ነው።

8ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤

የሰነፎች መሣለቂያ አታድርገኝ።

9ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣

ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም።

10ክንድህን አንሣልኝ፤

ከእጅህ ምት የተነሣ ደክሜአለሁና።

11ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤

ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤

በእርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ

12እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤

ጩኸቴን አድምጥ፤

ልቅሶዬንም ቸል አትበል፤

በአንተ ፊት እኔ መጻተኛ ነኝና፤

እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ።

13ላለመመለስ ከመሰናበቴ በፊት፣

ዳግመኛ ደስ ይለኝ ዘንድ ዐይንህን ከላዬ አንሣ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 39:1-13

第 39 篇

受苦者的呼求

大卫的诗,交给乐长耶杜顿。

1我说:“我要谨言慎行,

免犯口舌之罪。

只要身边有恶人,

我就用嚼环勒住自己的口。”

2然而,我默不作声,

连好话也不出口时,

内心就更加痛苦。

3我心如火烧,越沉思越烦躁,

便开口呼求:

4“耶和华啊,求你让我知道我人生的终点和寿数,

明白人生何其短暂。

5你使我的生命转瞬即逝,

我的岁月在你眼中不到片刻。

人的生命不过是一丝气息,(细拉)

6人生不过是幻影,

劳碌奔波却一场空,

积蓄财富却不知谁来享用。

7主啊,如今我盼望什么呢?

你是我的盼望。

8求你救我脱离一切过犯,

不要让愚昧人嘲笑我。

9我默然不语,一言不发,

因为我受的责罚是出于你。

10求你不要再惩罚我,

你的责打使我几乎丧命。

11因为人犯罪,你管教他们,

使他们所爱的被吞噬,像被虫蛀。

世人不过是一丝气息。(细拉)

12“耶和华啊,

求你垂听我的祷告,

倾听我的呼求,

别对我的眼泪视若无睹。

因为我在你面前只是客旅,

是寄居的,

正如我的祖先。

13求你宽恕我,

好让我在离世之前能重展笑容。”