መዝሙር 38 NASV - 诗篇 38 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 38:1-22

መዝሙር 38

የጭንቅ ሰዓት ጸሎት

የዳዊት መዝሙር፤ ለመታሰቢያ

1እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤

በመዓትህም አትቅጣኝ።

2ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና፤

እጅህም ተጭናኛለች።

3ከቍጣህ የተነሣ ሰውነቴ ጤና አጥቶአል፤

ከኀጢአቴም የተነሣ ዐጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።

4በደሌ ውጦኛል፤

እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል።

5ከንዝህላልነቴ የተነሣ፣

ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤

6ዐንገቴን ደፋሁ፤ ጐበጥሁም፤

ቀኑንም ሙሉ በትካዜ ተመላለስሁ።

7ወገቤ እንደ እሳት ነዶአል፤

ሰውነቴም ጤና የለውም።

8እጅግ ዝያለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤

ከልቤም መታወክ የተነሣ እጮኻለሁ።

9ጌታ ሆይ፤ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነው፤

ጭንቀቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

10ልቤ በኀይል ይመታል፤ ጒልበት ከድቶኛል፤

የዐይኔም ብርሃን ጠፍቶአል።

11ከቊስሌ የተነሣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ፤

ጎረቤቶቼም ርቀው ቆሙ።

12ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤

ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤

ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ።

13እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቈሮ፣

አፉንም መክፈት እንደማይችል ዲዳ ሆንሁ።

14በእርግጥም ጆሮው እንደማይሰማ፣

አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ።

15እግዚአብሔር ሆይ፤ በተስፋ እጠብቅሃለሁ፤

ጌታ አምላኬ ሆይ፤ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ።

16እኔ፣ “ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ አይበላቸው፤

እግሬም ሲንሸራተት፣ በላዬ አይኵራሩብኝ” ብያለሁና።

17ልወድቅ ተቃርቤአለሁ፤

ከሥቃዬም ከቶ አልተላቀቅሁም።

18በደሌን እናዘዛለሁ፤

ኀጢአቴም አውካኛለች።

19ብርቱዎች ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤

ያለ ምክንያት የሚጠሉኝም ስፍር ቊጥር የላቸውም።

20መልካሙን ስለ ተከተልሁ፣

በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ ጠሉኝ።

21እግዚአብሔር ሆይ፤ አትተወኝ፤

አምላኬ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።

22ጌታዬ መድኅኔ ሆይ፤

እኔን ለመርዳት ፍጠን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 38:1-22

第 38 篇

受苦者的祈求

大卫求上帝眷顾的诗。

1耶和华啊,

求你不要在发怒时惩罚我,

不要在烈怒下管教我。

2因为你的箭射穿我,

你的手击打我。

3你的怒气使我浑身是病,

我的罪恶使我骨头朽烂。

4我的罪恶滔天,使我不堪其重。

5我因愚昧而伤口溃烂流脓。

6我疼得弯腰驼背,

终日哀伤。

7我的腰灼痛难忍,

我浑身是病。

8我精疲力尽,彻底崩溃;

我心中悲伤,呻吟不止。

9主啊,你知道我的渴望,

听见了我的叹息。

10我的心砰砰直跳,

气力衰竭,

眼睛黯淡无光。

11因我的疾病,朋友同伴回避我,

亲人远离我。

12谋害我的人设下陷阱,

想害我的人威胁我,

整天图谋奸计。

13但我像听不见的聋子,

无法说话的哑巴。

14我就像一个不能听、不能辩的人。

15耶和华啊,我等候你;

主,我的上帝啊,你必应允我。

16我曾求告你,

别让他们幸灾乐祸,

在我失脚时沾沾自喜。

17我快要跌倒,

我的痛苦无休无止。

18我要承认我的罪过,

罪恶使我心里惴惴不安。

19我的仇敌势力强大,

无故恨我的人不计其数。

20我追求良善,

他们就恨我,以恶报善。

21耶和华啊,求你不要撇弃我!

我的上帝啊,求你不要远离我!

22拯救我的主啊,

求你快来帮助我!