መዝሙር 30 NASV - 诗篇 30 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 30:1-12

መዝሙር 30

ከክፉ አደጋ የዳነ ሰው ምስጋና

ለቤተ መቅደሱ ምረቃ የተዘመረ፤ የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ከታች አንሥተኸኛልና፣

ጠላቶቼም በላዬ እንዳይደሰቱ አድርገሃልና፣

ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።

2እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ ጮኽሁ፤

አንተም ፈወስኸኝ።

3እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን ከሲኦል30፥3 ወይም ከመቃብር አወጣሃት፤

ወደ ጒድጓድ ከመውረድም መልሰህ ሕያው አደረግኸኝ።

4እናንተ ቅዱሳኑ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤

ቅዱስ ስሙንም አወድሱ።

5ቊጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤

ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤

ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣

በማለዳ ደስታ ይመጣል።

6እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣

“ከቶ አልናወጥም” አልሁ።

7እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣

ተራሮቼ30፥7 ወይም ኰረብታማ የሆነች አገሬ ጸኑ፣

ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣

ውስጤ ታወከ።

8እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤

ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤

9“በእኔ ወደ ጒድጓድ መውረድ፣

በመሞቴ ምን ጥቅም ይገኛል?30፥9 ወይም ዝም ብል … ይገኛል?

ዐፈር ያመሰግንሃልን?

ታማኝነትህንስ ይናገራልን?

10እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማ፤ ማረኝም፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ ረዳት ሁነኝ።”

11ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ፤

ማቄን አውልቀህ ፍስሓን አለበስኸኝ፤

12እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 30:1-12

第 30 篇

感恩的祷告

大卫的诗,作献殿之歌。

1耶和华啊,我要赞美你,

因为你救我脱离危难,

不让我的仇敌幸灾乐祸。

2我的上帝耶和华啊,

我呼求你,你就医治了我。

3耶和华啊,你从阴间把我救出,

没有让我落入坟墓。

4耶和华忠心的子民啊,

你们要歌颂祂,

赞美祂的圣名。

5因为祂的怒气瞬间消逝,

祂的恩惠却持续一生。

我们虽然整夜哭泣,

早晨必定欢呼。

6我在顺境中曾说:

“我永不动摇。”

7耶和华啊,

你向我施恩,我便稳固如山;

你掩面不理我,我就惊慌失措。

8耶和华啊,我向你呼求,

恳求你怜悯,说:

9“耶和华啊,

我被毁灭、落入坟墓有何益处?

我归于尘土,还能赞美你、

宣扬你的信实吗?

10耶和华啊,求你垂听我的呼求,怜悯我!

耶和华啊,求你帮助我!”

11你把我的哀哭变成了舞步,

为我脱下悲伤的麻衣,

披上喜乐的外袍,

12好叫我从心底歌颂你,

不致默然无声。

我的上帝耶和华啊,

我要永远向你感恩!