መዝሙር 3 NASV - 诗篇 3 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 3:1-8

መዝሙር 3

የመከራ ተቀባዩ የጧት ጸሎት

ዳዊት ከልጁ ከአቤሰሎም በሸሸ ጊዜ የዘመረው መዝሙር

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ

ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ!

2ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር

አይታደግሽም” አሏት። ሴላ3፥2 በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ በተደጋጋሚ የሚገኝ ሲሆን የቃሉ ትርጒም በትክክል አይታወቅም፤ የሙዚቃ ምልክት ሳይሆን አይቀርም

3እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን

የምትከልል ጋሻ ነህ፤

ክብሬና፣ ራሴንም ቀና ቀና

የምታደርግ አንተ ነህ።3፥3 ወይም እግዚአብሔር … ወደ ላይ የምታነሣ ክብሬ ሆይ

4ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ፤

እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ

5እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤

እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ።

6በየአቅጣጫው የከበበኝን፣

አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።

7እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ!

አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤

የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤

የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ።

8ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤

በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 3:1-8

第 3 篇

求助的早祷

大卫逃避儿子押沙龙时作的诗。

1耶和华啊,我的敌人何其多!

反对我的人何其多!

2他们都说上帝不会来救我。(细拉)3:2 细拉”语意不明,常在诗篇中出现,可能是一种音乐术语。

3可是,耶和华啊!

你是四面保护我的盾牌,

你赐我荣耀,使我昂首而立。

4我向耶和华呼求,

祂就从祂的圣山上回应我。(细拉)

5我躺下,我睡觉,我醒来,

都蒙耶和华看顾。

6我虽被千万仇敌围困,

也不会惧怕。

7耶和华啊,求你起来!

我的上帝啊,求你救我!

求你掴我一切仇敌的脸,

打碎恶人的牙齿。

8耶和华啊,你是拯救者,

愿你赐福你的子民!(细拉)