መዝሙር 29 NASV - 诗篇 29 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 29:1-11

መዝሙር 29

ለማዕበሉ ጌታ የቀረበ ውዳሴ

የዳዊት መዝሙር

1እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤

ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።

2ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤

በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ።

3የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤

የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤

እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።

4የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤

የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው።

5የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤

እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል።

6ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣

ስርዮንንም29፥6 አርሞንዔም የተባለው ተራራ ነው። እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።

7የእግዚአብሔር ድምፅ

የእሳት ነበልባል ይረጫል።

8የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤

የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።

9የእግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤29፥9 ወይም እግዚአብሔር አጋዘን እንድትወልድ ያደርጋል

ጫካዎችንም ይመነጥራል፤

ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።

10እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጦአል፤29፥10 ወይም ይቀመጣል

እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።

11እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤

እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 29:1-11

第 29 篇

上帝威严的声音

大卫的诗。

1上帝的众子啊,

要赞美耶和华,

赞美祂的荣耀和能力,

2要赞美祂荣耀的名,

穿上圣洁的衣服敬拜祂。

3耶和华的声音回荡在海上,

荣耀的上帝打雷,

在洪涛之上打雷。

4耶和华的声音充满能力;

耶和华的声音充满威严。

5耶和华的声音震断香柏树,

耶和华劈碎黎巴嫩的香柏树,

6使黎巴嫩山跳跃如小牛,

西连山跳跃如野牛。

7耶和华的声音携闪电而来,

8震动旷野,

震动加低斯的旷野。

9耶和华的声音击倒橡树29:9 击倒橡树”或译“使母鹿生产”。

使树木凋零。

众人在祂殿中高呼:

“荣耀归于耶和华!”

10耶和华坐在洪涛之上,

耶和华永远坐着为王。

11耶和华赐力量给自己的子民,

赐给他们平安的福乐。