መዝሙር 28 NASV - 诗篇 28 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 28:1-9

መዝሙር 28

ልመናና ምስጋና

የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤

ዐለቴ ሆይ፤ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ፤

አንተ ዝም ካልኸኝ፤

ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱ እሆናለሁ።

2ለርዳታ በጮኽሁ ጊዜ፣

ወደ ቅዱስ ማደሪያህ፣

እጆቼን በዘረጋሁ ጊዜ፣

የልመናዬን ቃል ስማ።

3በልባቸው ተንኰል እያለ፣

ከባልንጀሮቻቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ፣

ከክፉ አድራጊዎችና፣

ከዐመፃ ሰዎች ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ።

4እንደ ሥራቸው፣

እንደ ክፉ ተግባራቸው ክፈላቸው፤

እንደ እጃቸው ሥራ ስጣቸው፤

አጸፋውን መልስላቸው።

5ለእግዚአብሔር ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣

ለእጆቹም ተግባራት ስፍራ ስላልሰጡ፣

እርሱ ያፈርሳቸዋል፤

መልሶም አይገነባቸውም።

6የልመናዬን ቃል ሰምቶአልና፣

እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን።

7እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤

ልቤ በእርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤

ልቤ ሐሤት አደረገ፤

በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።

8እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤

ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።

9ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤

እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 28:1-9

第 28 篇

祈求上帝帮助

大卫的诗。

1耶和华啊,我呼求你;

我的磐石啊,别不理我。

你若默然不语,

我必绝望而死。

2我向你呼求,

向你的至圣所举手祷告时,

求你垂听。

3求你不要把我与奸恶人一同责罚,

他们对邻居口蜜腹剑。

4求你使他们罪有应得,

按他们的恶行,

按他们手上的罪恶报应他们。

5他们既然毫不在意耶和华的作为和祂的创造,

祂必永远毁灭他们。

6耶和华当受称颂!

因为祂听了我的恳求。

7祂是我的力量,我的盾牌,

我信靠祂,就得帮助。

我的心欢喜雀跃,

我要歌唱赞美祂。

8耶和华是祂子民的力量,

是祂膏立者得救的堡垒。

9耶和华啊,

求你拯救你的子民,

赐福给你拣选的人,

如牧人般照顾他们,

永远扶持他们。