መዝሙር 26 NASV - 诗篇 26 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 26:1-12

መዝሙር 26

የንጹሕ ሰው ጸሎት

የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣

አንተው ፍረድልኝ።

ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣

በእግዚአብሔር ታምኛለሁ።

2እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤

መርምረኝም፤

ልቤንና ውስጤን መርምር፤

3ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣

በእውነትህም ተመላለስሁ።

4ከማይረቡ ጋር አልተቀመጥሁም፤

ከግብዞችም ጋር አልተባበርሁም።

5የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤

ከዐመፀኞችም ጋር አልቀመጥም።

6እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤

7የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣

ታምራትህንም አወራ ዘንድ ነው።

8እግዚአብሔር ሆይ፤ የምትኖርበትን ቤት፣

የክብርህን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።

9ነፍሴን ከኀጢአተኞች ጋር፣

ሕይወቴንም ከደም አፍሳሾች ጋር አታስወግዳት።

10በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ፤

ቀኝ እጃቸውም ጒቦን ያጋብሳል።

11እኔ ግን በተአማኒ ሕይወት እጓዛለሁ፤

አድነኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ።

12እግሮቼ በደልዳላ ስፍራ ቆመዋል፤

በታላቅ ጉባኤ መካከልም እግዚአብሔርን እባርከዋለሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 26:1-12

第 26 篇

义人的祈求

大卫的诗。

1耶和华啊,求你为我申冤,

因为我行为纯全,

毫不动摇地信靠你。

2耶和华啊,求你察验我,

试炼我,鉴察我的心思意念。

3因为我铭记你的慈爱,

我行在你的真理中。

4我没有与诡诈者为伍,

没有跟虚伪之人同流。

5我憎恨奸恶之辈,

不愿与恶人交往。

6耶和华啊,我洗手表明清白,

再走到你的坛前,

7高唱感恩之歌,

述说你的一切奇妙作为。

8耶和华啊,我爱你的殿,

你荣耀充满的地方。

9别把我的灵魂和罪人同毁,

别把我的性命与嗜血之徒同灭。

10他们满腹奸计,收受贿赂。

11但我行为纯全,

求你施恩拯救我。

12我站在平安之地,

我要在众人面前赞美耶和华。