መዝሙር 25 NASV - 诗篇 25 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 25:1-22

መዝሙር 2525፥0 25 ይህ መዝሙር እያንዳንዱ ጥቅስ ተከታታይ ፊደላት ባሉት የዕብራይስጥ ሆህያት የሚጀምር፣ ጅማሬው ወይም ጅማሬውና መጨረሻው ትርጒም የሚሰጥ ግጥም ነው።

በአደጋ ጊዜ የቀረበ ጸሎት

የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁ፤

2አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤

እባክህ አታሳፍረኝ፤

ጠላቶቼም አይዘባነኑብኝ።

3አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣

ከቶ አያፍሩም፤

ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣

ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ።

4እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤

መንገድህንም አስተምረኝ።

5አንተ አዳኜ፣ አምላኬም ነህና፣

በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤

ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።

6እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህንና ፍቅርህን አስብ፤

እነዚህ ከጥንት የነበሩ ናቸውና።

7የልጅነቴን ኀጢአት፣

መተላለፌንም አታስብብኝ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣

እንደ ምሕረትህም መጠን ዐስበኝ።

8እግዚአብሔር መልካምና ቅን ነው፤

ስለዚህ ኀጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።

9ዝቅ ያሉትን በፍትሕ ይመራቸዋል፤

ለትሑታንም መንገዱን ያስተምራቸዋል።

10ኪዳኑንና ሥርዐቱን ለሚጠብቁ፣

የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ናቸው።

11እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣

ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ።

12እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው?

በተመረጠለት መንገድ ያስተምረዋል።

13ዘመኑን በተድላ ደስታ ያሳልፋል፤

ዘሩም ምድርን ይወርሳል።

14እግዚአብሔር ምስጢሩን ከሚፈሩት ወዳጆቹ አይሰውርም፤

ኪዳኑንም ይገልጥላቸዋል።

15ዐይኖቼ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤

እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።

16እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣

ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ።

17የልቤ መከራ በዝቶአል፤

ከጭንቀቴ ገላግለኝ።

18ጭንቀቴንና መከራዬን ተመልከት፤

ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።

19ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ ተመልከት፤

እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ።

20ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም፤

መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ።

21አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣

ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ።

22አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን፣

ከመከራው ሁሉ አድነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 25:1-22

第 25 篇

祈求引导和赦免

大卫的诗。

1耶和华啊,我的心仰望你。

2我的上帝啊,我信靠你,

求你不要叫我蒙羞,

不要让我的仇敌胜过我。

3信靠你的必不羞愧,

背信弃义者必蒙羞。

4耶和华啊,

求你指引我走你的路,

教导我行你的道。

5求你以你的真理引领我,

教导我,因为你是拯救我的上帝,

我日夜仰望你。

6耶和华啊,

求你顾念你亘古以来常施的怜悯和慈爱,

7求你饶恕我年轻时的罪恶和过犯,

以你的恩惠和慈爱待我。

8耶和华良善公正,

祂教导罪人走正路,

9指引谦卑人追求公义,

教导他们行祂的道。

10遵守祂的约和法度的人,

耶和华以慈爱和信实相待。

11耶和华啊,我罪恶深重,

求你为了自己的名而赦免我。

12凡敬畏耶和华的人,

耶和华必指示他当走的路。

13他必享福,

他的后代必承受土地。

14耶和华与敬畏祂的人为友,

使他们认识祂的约。

15我常常仰望耶和华,

因为唯有祂能救我脱离网罗。

16耶和华啊,我孤苦零丁,

求你眷顾我,恩待我。

17我心中充满愁烦,

求你救我脱离患难。

18求你体恤我的忧伤和痛苦,

赦免我的罪恶。

19看啊,我的仇敌众多,

他们都痛恨我。

20求你保护、搭救我的性命,

别让我蒙羞,因为我投靠你。

21求你以诚实和正义护卫我,

因为我仰望你。

22上帝啊,

求你救赎以色列脱离一切困境。