መዝሙር 24 NASV - 诗篇 24 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 24:1-10

መዝሙር 24

ወደ መቅደስ መግቢያ ጸሎት

የዳዊት መዝሙር

1ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ፣

ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤

2እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፤

በውሆችም ላይ አጽንቶአታል።

3ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ሊወጣ ይችላል?

በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?

4ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤

ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤

በውሸት የማይምል፤24፥4 ወይም በሐሰትም ያልማለ

5እርሱ በረከትን ከእግዚአብሔር ዘንድ፣

ምሕረትንም ከአዳኝ አምላኩ ይቀበላል።

6እርሱን የሚፈልግ ትውልድ እንዲህ ነው፤

የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ፊትህን24፥6 ሁለት የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆችና ሱርስት (እንዲሁም ሰብዓ ሊቃናት ይመ) እንዲሁ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች ግን ያዕቆብ፤ ፊትህን …  የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው። ሴላ

7እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤

እናንተ የዘላለም በሮች፤

የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!

8ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?

እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኀያል፤

እግዚአብሔር ነው በውጊያ ኀያል።

9እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤

እናንተ የዘላለም በሮች፤

የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!

10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?

የሰራዊት አምላክ

እርሱ የክብር ንጉሥ ነው። ሴላ

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 24:1-10

第 24 篇

荣耀的君王

大卫的诗。

1大地和其中的万物都属于耶和华,

世上的一切都是祂的。

2祂把大地奠基于海中,

建立在大水之上。

3谁能登耶和华的山?

谁能站在祂的圣所中?

4只有那些手洁心清,

不拜假神,不起假誓的人。

5他们必蒙耶和华赐福,

被救他们的上帝称为义人。

6这就是寻求耶和华的人,

他们敬拜雅各的上帝。(细拉)

7众城门啊,打开吧!

古老的城门啊,敞开吧!

让荣耀的君王进来。

8谁是荣耀的君王呢?是耶和华,

祂强大无比、战无不胜。

9众城门啊,打开吧!

古老的城门啊,敞开吧!

让荣耀的君王进来。

10谁是荣耀的君王呢?

万军之耶和华是荣耀的君王。(细拉)