መዝሙር 23 NASV - 诗篇 23 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 23:1-6

መዝሙር 23

መልካሙ እረኛ

የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤

አንዳች አይጐድልብኝም።

2በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤

በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤

3ነፍሴንም ይመልሳታል።

ስለ ስሙም፣

በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።

4በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ፤23፥4 ወይም እጅግ ጨለማ በሆነው ሸለቆ ውስጥ

ብሄድ እንኳ፣

አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ፣

ክፉን አልፈራም፤

በትርህና ምርኵዝህ፣

እነርሱ ያጽናኑኛል።

5ጠላቶቼ እያዩ፣

በፊቴ ማዕድ አዘጋጀህልኝ፤

ራሴን በዘይት ቀባህ፤

ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል።

6በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣

በጎነትና ምሕረት በእርግጥ ይከተሉኛል፤

እኔም በእግዚአብሔር ቤት፣

ለዘላለም እኖራለሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 23:1-6

第 23 篇

耶和华是我的牧者

大卫的诗。

1耶和华是我的牧者,

我必一无所缺。

2祂让我安歇在青草地上,

领我到幽静的溪水旁。

3祂使我的心灵苏醒,

为了自己的名引导我走正路。

4我纵使走过死亡的幽谷,

也不怕遭害,

因为你与我同在,

你的杖和竿带给我安慰。

5在我敌人面前你为我摆设宴席,

又用膏油浇我的头,

使我恩福满溢。

6你的恩惠和慈爱必伴随我一生,

我要永远住在你的殿中。