መዝሙር 22 NASV - 诗篇 22 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 22:1-31

መዝሙር 22

የጻድቅ ሰው መከራና ተስፋ

ለመዘምራን አለቃ፤ በ“ንጋት አጋዘን” ዜማ የሚዜም፤ የዳዊት መዝሙር

1አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?

እኔን ከማዳን፣

ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?

2አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ አጮኻለሁ፤

አንተ ግን አልመለስህልኝም፤

በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።

3አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤22፥3 ወይም አንተ ግን ቅዱስ ነህ፤ በእስራኤል ምሥጋና ላይ በዙፋን ተቀምጠሃል

የእስራኤልም ምስጋና ነህ።

4አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤

ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው።

5ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤

በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።

6እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤

ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።

7የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤

ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤

8በእግዚአብሔር ተማምኖአል፤

እንግዲህ እርሱ ያድነው፤

ደስ የተሰኘበትን፣

እስቲ ይታደገው።”

9አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤

በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።

10ከማሕፀን ስወጣም በአንተ ላይ ተጣልሁ፤

ከእናቴ ሆድ ጀምሮም አንተ አምላኬ ነህ።

11መከራ እየተቃረበ ነውና፣

የሚረዳኝም የለምና፣

ከእኔ አትራቅ።

12ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤

ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።

13እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ፣

አፋቸውን ከፈቱብኝ።

14እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤

ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤

ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤

በውስጤም ቀለጠ።

15ጒልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤

ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤

ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ።22፥15 ወይም … ዐፈር ውስጥ ተኛኹኝ

16ውሾች ከበቡኝ፤

የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፎአል፤

እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።22፥16 አንዳንድ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች፣ ሰብዓ ሊቃናትና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች እንደ አንበሳ፣ ይላሉ።

17ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤

እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።

18ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤

በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።

19አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤

አጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

20ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤

ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።

21ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤

ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።22፥21 ወይም ሰምተኸኛል

22ስምህን ለወንድሞቼ እነግራለሁ፤

በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።

23እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤

አወድሱት፤

እናንተ የያቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤

የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት።

24እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣

አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤

ፊቱንም ከእርሱ አልሰወረም፤

ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው።

25በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤

እርሱን በሚፈሩት22፥25 ዕብራይስጡ እኔ በሚፈሩኝ ይላል። ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ።

26ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤

እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤

ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!

27የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤

ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤

የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣

በፊቱ ይሰግዳሉ።

28መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤

ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው።

29የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤

ይሰግዱለታልም፤

ነፍሱን በሕይወት ማቆየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር፣

ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል።

30የኋለኛው ትውልድ ያገለግለዋል፤

ለመጪው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል።

31ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣

ጽድቁን ይነግራሉ፤

እርሱ ይህን አድርጎአልና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 22:1-31

第 22 篇

苦难中的呼求和感恩

大卫的诗,交给乐长,调用“朝鹿”。

1我的上帝,我的上帝,

你为何离弃我?

为何迟迟不来救我,

不听我的哀号呢?

2我的上帝啊,

我日夜不停地呼求,

你却没有回应。

3然而,你是圣洁的,

你的宝座设立在以色列人的颂赞之上。

4我们的祖先信靠你,

他们信靠你,

你就拯救他们。

5他们向你呼求,

就得到拯救;

他们信靠你,

就不会失望。

6但我好像不是人,只是一条虫,

受尽人的羞辱和藐视。

7看见我的人都讥笑我,

他们撇着嘴、摇着头说:

8“他信靠耶和华,

让耶和华救他吧!

既然耶和华喜悦他,

让耶和华拯救他吧!”

9耶和华啊,

是你使我从母腹中安然出生,

让我在母亲怀里便倚靠你。

10我一出生就被交托在你手中,

你从我出母胎就是我的上帝。

11求你不要远离我,

因为危难当头,无人帮我。

12我被许多仇敌围困,

他们像巴珊的公牛那样强壮。

13他们张口要吞噬我,

如同吼叫着撕食猎物的狮子。

14我的力量如水消逝,

我的骨头都脱了节,

我的心如蜡熔化。

15我的力量枯竭如焦土,

我的舌头发干紧贴上颚。

你把我放在死亡的尘土中。

16恶人包围我,犹如一群恶犬,

他们刺伤我的手脚。

17我身上的骨头历历可见,

人们都幸灾乐祸地看着我。

18他们分我的外衣,

又为我的内衣抽签。

19耶和华啊,求你不要远离我。

你是我的力量,

求你快来帮助我。

20求你救我逃脱刀剑之灾,

从这些恶犬的利爪下拯救我的生命。

21求你救我脱离狮子的口,

使我脱离野牛的角。

22我要向众弟兄传扬你的名,

在会众当中赞美你。

23敬畏耶和华的人啊,

你们都要赞美祂,

雅各的后裔都要尊崇祂的名,

以色列的后裔都要敬畏祂。

24因为祂没有藐视、厌恶苦难中的人,

也没有掩面不顾他们,

而是垂听他们的呼求。

25我要在大会中赞美你,

在敬畏你的人面前履行我的誓言。

26穷苦人必得饱足,

寻求耶和华的人必赞美祂,

他们的心要永远欢欣跳跃。

27普世都要心系耶和华,归向祂,

各国人民都要敬拜祂。

28因为耶和华是主宰,

祂统治列国。

29世上的富贵人要敬拜祂,

必归尘土的世人都要敬拜祂。

30世世代代的人都要事奉祂,

传扬主所行的奇事。

31他们也要向未来的世代传讲祂的公义作为。