መዝሙር 20 NASV - 诗篇 20 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 20:1-9

መዝሙር 20

ጸሎት ለንጉሡ

ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤

የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።

2ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ፤

ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።

3ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤

የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ። ሴላ

4የልብህን መሻት ይስጥህ፤

ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ።

5በአንተ ድል ደስ ይበለን፤

በአምላካችን ስም አርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤

እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ።

6እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድን

አሁን ዐወቅሁ፤

የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣

ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።

7እነዚህ በሰረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤

እኛ ግን ትምክህታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።

8እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤

እኛ ግን ተነሣን፤ ጸንተንም ቆምን።

9እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥን አድን፤

እኛም በጠራንህ ቀን ስማን።20፥9 ወይም አድን! ንጉሥ ሆይ፤ ስማን

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 20:1-9

第 20 篇

祈求胜利

大卫的诗,交给乐长。

1愿耶和华应允你患难时的呼求。

雅各的上帝保护你。

2愿祂从圣所帮助你,

锡安山扶持你。

3愿祂喜悦你献的祭物,

悦纳你的燔祭。(细拉)

4愿祂使你心愿得偿、

计划实现。

5我们要因你得胜而高声欢唱,

高举耶和华的旌旗。

愿耶和华答应你一切的祈求。

6现在我知道耶和华拯救祂膏立的王,

祂从圣天之上应允他,

用右手的大能拯救他。

7有人靠战车,有人靠战马,

但我们靠的是我们的上帝耶和华的名。

8他们都一败涂地,

我们却屹立不倒。

9耶和华啊,求你拯救你立的王。

我们呼求的时候,

求你垂听。