መዝሙር 19 NASV - 诗篇 19 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 19:1-14

መዝሙር 19

እግዚአብሔር የጽድቅ ፀሓይ

ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር

1ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤

የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ።

2ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤

ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤

3ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤

ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም።19፥3 ወይም የሚናገሩት የላቸውም፤ ቃላት የለም፤ ከእርሱ ምንም ድምፅ አይሰማም

4ያም ሆኖ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፣

ቃላቸውም19፥4 ሰብዓ ሊቃናት የሩምና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ ዕብራይስጡ ግን ድንበራቸው ይላል። እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል።

እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሎአል፤

5ፀሓይም ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል፤

ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል።

6መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤

ዑደቱም እስከ ሌላኛው ዳርቻ ነው፤

ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።

7የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤

ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤

የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤

አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል።

8የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤

ልብን ደስ ያሰኛሉ።

የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤

ዐይንን ያበራል።

9እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤

ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣

ሁለንተናውም ጻድቅ ነው፤

10ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣

እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤

ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤

ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል።

11ደግሞም አገልጋይህ በእርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤

እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው።

12ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል?

ከተሰወረ በደል አንጻኝ።

13ባሪያህን ከድፍረት ኀጢአት ጠብቅ፤

እንዳይሠለጥንብኝም ርዳኝ፤

ያን ጊዜ ያለ እንከን እሆናለሁ፤

ከታላቅ በደልም እነጻለሁ።

14መጠጊያዬና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤

የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣

በፊትህ ያማረ ይሁን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 19:1-14

第 19 篇

上帝的作为和律法

大卫的诗,交给乐长。

1诸天述说上帝的荣耀,

穹苍传扬祂的作为。

2它们日复一日地诉说,

夜复一夜地宣扬,

3无言无语,无声无息。

4它们的声音传遍天下,

它们的话语传到地极。

上帝在天上为太阳设立居所。

5太阳出来时,如步出洞房的新郎,

又如欢然奔跑赛程的健儿。

6它滑过长空,

从天这边绕到天那边,

热量广及万物。

7耶和华的律法完美,

能更新生命;

耶和华的法度可靠,

让愚人有智慧。

8耶和华的法则公正,

使人充满喜乐;

耶和华的命令纯全,

让人眼目明亮。

9要以纯洁的心敬畏耶和华,

直到永远;

耶和华的法令可靠,

全然公义。

10这些比纯金还宝贵,

比蜂房的蜜更甘甜。

11你仆人从中受到警戒,

遵守的人必得大赏赐。

12谁能知道自己的过失呢?

求你赦免我心中隐藏的过错。

13求你拦阻我,

别让我明知故犯,

别让罪恶辖制我。

这样,我才纯全正直,

免犯大过。

14耶和华——我的磐石、我的救赎主啊,

愿你喜悦我口中的言语、心中的意念。