መዝሙር 149 NASV - 诗篇 149 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 149:1-9

መዝሙር 149

የድል መዝሙር

1ሃሌ ሉያ።149፥1 አንዳንዶች ከቍ 9 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤

ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ።

2እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤

የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ።

3ስሙን በሽብሰባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት።

4እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤

የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።

5ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤

በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።

6የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣

ባለ ሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤

7በዚህ ሕዝቦችን ይበቀላሉ፤

ሰዎችንም ይቀጣሉ፤

8ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣

መኳንንታቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፤

9ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው።

ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት።

ሃሌ ሉያ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 149:1-9

第 149 篇

以色列要赞美上帝

1你们要赞美耶和华!

要向耶和华唱新歌,

在祂忠心子民的聚会中颂赞祂!

2以色列因他的造物主而欢喜,

锡安的百姓因他们的君王而快乐。

3愿他们跳舞赞美祂的名,

击鼓弹琴歌颂祂。

4因为耶和华喜爱祂的子民,

祂赐尊荣给谦卑的人,

使他们得胜。

5愿祂忠心的子民因所得的荣耀而欢乐,

愿他们躺卧在床上的时候也欢唱。

6-7愿他们高声颂赞耶和华,

手握两刃利剑向列国复仇,

在列邦中施行惩罚,

8用铁链捆绑他们的君王,

用铁铐锁住他们的首领,

9按他们的罪状审判他们。

这就是祂忠心的子民所得的荣耀。

你们要赞美耶和华!