መዝሙር 148 NASV - 诗篇 148 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 148:1-14

መዝሙር 148

ፍጥረተ ዓለም ሁሉ ያመስግን

1ሃሌ ሉያ።148፥1 አንዳንዶች ከቍ 14 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤

በላይ በአርያም አመስግኑት።

2መላእክቱ ሁሉ አመስግኑት፤

ሰራዊቱ ሁሉ አመስግኑት፤

3ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤

የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት።

4ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤

ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት።

5እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣

የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።

6ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤

የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።

7የባሕር ውስጥ ግዙፍ ፍጥረትና ጥልቅ ውሆች ሁሉ፣

እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት።

8እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣

ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣

9ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፣

የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ፣

10የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣

በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበሩ ወፎችም፣

11የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣

መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣

12ወጣት ወንዶችና ደናግል፣

አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት።

13ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣

ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣

እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ።

14እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን148፥14 ቀንድ የጥንካሬ ትእምርት ሲሆን ንጉሥን ያመለክታል። አስነሥቶአል፤

ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣

እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች።

ሃሌ ሉያ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 148:1-14

第 148 篇

万物当赞美上帝

1你们要赞美耶和华!

从天上赞美祂,

在高天赞美祂!

2众天使啊,你们要赞美祂!

众天军啊,你们要赞美祂!

3太阳、月亮啊,你们要赞美祂!

闪亮的星辰啊,你们要赞美祂!

4高天啊,你要赞美祂!

穹苍之上的水啊,你要赞美祂!

5愿这一切都来赞美耶和华!

因为祂一发命令便创造了万物。

6祂使这一切各处其位,

永不改变,

祂的命令永不废弃。

7要在世上赞美耶和华,

海中的巨兽和深渊啊,

8火焰、冰雹、雪花、云霞和听祂吩咐的狂风啊,

9高山、丘陵、果树和香柏树啊,

10野兽、牲畜、爬虫和飞鸟啊,

11世上的君王、万国、首领和审判官啊,

12少男、少女、老人和孩童啊,

你们要赞美耶和华!

13愿他们都赞美耶和华,

因为唯有祂的名当受尊崇,

祂的荣耀在天地之上。

14祂使自己的子民强盛,

叫祂忠心的子民,

祂心爱的以色列人得到尊荣。

你们要赞美耶和华!