መዝሙር 146 NASV - 诗篇 146 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 146:1-10

መዝሙር 146

ለረድኤት አምላክ ምስጋና

1ሃሌ ሉያ።146፥1 አንዳንዶች ከ10 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።

2በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን

አመሰግናለሁ፤

በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።

3በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ ሥጋ ለባሾችም አትመኩ።

4መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤

ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።

5ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣

ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው ምስጉን ነው፤

6እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣

በእነዚህም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ፣

ታማኝነቱንም ለዘላለም የሚጠብቅ ነው፤

7ለተበደሉት የሚፈርድ፣

ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤

እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤

8እግዚአብሔር የዕዉራንን ዐይን ያበራል፤

እግዚአብሔር የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋል፤

እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወዳል፤

9እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤

ድኻ ዐደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤

የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።

10እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤

ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው።

ሃሌ ሉያ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 146:1-10

第 146 篇

赞美上帝的帮助

1你们要赞美耶和华!

我的心啊,你要赞美耶和华。

2我要一生赞美耶和华,

我一息尚存都要赞美祂。

3你们不要倚靠权贵,

不要倚靠世人,

他们救不了你们。

4他们气息一断,便归回尘土,

他们的打算转眼成空。

5雅各的上帝相助、仰望上帝耶和华的人有福了!

6耶和华创造了天、地、海和其中的万物,

祂永远信实可靠。

7祂为受压制的人申冤,

赐食物给饥饿的人,

使被囚者得自由。

8耶和华叫瞎子看见,

扶持被重担所压的人,

祂喜爱义人。

9耶和华保护寄居异地的人,

看顾孤儿寡妇,

祂挫败恶人的阴谋诡计。

10耶和华永远掌权。

锡安啊,

你的上帝要世世代代做王。

你们要赞美耶和华!