መዝሙር 145 NASV - 诗篇 145 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 145:1-21

መዝሙር 145145፥0 ይህ መዝሙር ተከታታይ በሆኑ የዕብራይስጥ ፊደላት የሚጀምር ሲሆን (ከቍ 13 ጭምር) መነሻዎቹ ወይም መነሻዎቹና መድረሻዎቹ ሆህያት ቍልቍል ሲነበቡ ትርጒም ያላቸውን ቃላት የሚፈጥሩ ናቸው።

ምስጋና ለንጉሡ ለእግዚአብሔር

የዳዊት የምስጋና መዝሙር

1አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤

ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።

2በየቀኑ እባርክሃለሁ፤

ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ።

3እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤

ታላቅነቱም አይመረመርም።

4ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤

ብርቱ ሥራህን ያውጃል።

5ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤

ስለ ድንቅ ሥራህም145፥5 የሙት ባሕር ጥቅልሎች እና ሱርስት (የሰብዓ ሊቃናትን ትርጒም ይመ) ስለ ግርማህ ታላቅነትና ክብር፣ ዕፁብ ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ ይላሉ። ያወራሉ።

6ስለ ድንቅ ሥራህ ብርታት ይነጋገራሉ፤

እኔም ስለ ታላቅነትህ ዐውጃለሁ።

7የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤

ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።

8እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው፤

ለቍጣ የዘገየ፣ ምሕረቱ የበዛ።

9እግዚአብሔር ለሁሉ ቸር ነው፤

ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው።

10እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግንሃል፤

ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።

11ስለ መንግሥትህ ክብር ይናገራሉ፤

ስለ ኀይልህም ይነጋገራሉ፤

12በዚህም ብርቱ ሥራህን፣

የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቃሉ።

13መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፤

ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል።

እግዚአብሔር ቃሉን ሁሉ ይጠብቃል፤

በሥራውም145፥13 አንድ የማስሬቲክ ቅጅ፣ የሙት ባሕር ጥቅልሎች እና ሱርስት (የሰብዓ ሊቃናትን ትርጒም ይመ) እንዲሁም አብዛኛው የማስሬቲክ ቅጆች የቍ 13 ሁለት ስንኞች የሏቸውም። ሁሉ ቸር ነው።

14እግዚአብሔር የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል፤

የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል።

15የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤

አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።

16አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤

የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።

17እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣

በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

18እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣

በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።

19ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤

ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።

20እግዚአብሔር የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤

ክፉዎችን ሁሉ ግን ያጠፋል።

21አፌ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል፤

ፍጡር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ቅዱስ ስሙን ይባርክ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 145:1-21

第 145 篇

赞美之歌

大卫的赞美诗。

1我的上帝,我的王啊!

我要尊崇你,

我要永永远远称颂你的名。

2我要天天称颂你,

永永远远赞美你的名。

3耶和华是伟大的,

当受至高的颂赞,

祂的伟大无法测度。

4愿世世代代颂赞你的事迹,

传扬你大能的作为。

5我要默想你的荣耀、威严和奇妙作为。

6人们要述说你令人敬畏的大能作为,

我也要传扬你的伟大事迹。

7他们要诉说你的厚恩,

歌颂你的公义。

8耶和华有恩典和怜悯,

不轻易发怒,充满慈爱。

9耶和华善待万民,

怜悯祂所造的万物。

10耶和华啊,

你所创造的万物都要称谢你,

你忠心的子民也要称颂你。

11他们要述说你国度的荣耀,

讲论你的大能,

12好让世人知道你大能的作为和你国度的威严与荣耀。

13你的国度永远长存,

你的统治直到万代。

耶和华信守自己的一切应许,

以慈爱待祂所创造的万物。145:13 耶和华信守……万物”许多手抄本无此句。

14耶和华扶起跌倒的人,

扶持被重担所压的人。

15世人都仰赖你,

你按时赐给他们所需的食物。

16你慷慨满足一切生命的需要。

17耶和华的作为公义,

祂所行的充满慈爱。

18耶和华垂顾一切求告祂的人,

一切诚心求告祂的人。

19祂使敬畏祂的人心愿得偿,

垂听他们的呼求,拯救他们。

20耶和华保护所有爱祂的人,

毁灭一切恶人。

21我要开口赞美耶和华,

万物都要称颂祂的圣名,

直到永永远远。