መዝሙር 144 NASV - 诗篇 144 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 144:1-15

መዝሙር 144

የጦርነት መዝሙር

የዳዊት መዝሙር

1እጆቼን ለጦርነት፣ ጣቶቼን ለውጊያ የሚያሠለጥን፣

እግዚአብሔር ዐለቴ ይባረክ።

2እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤

ምሽጌና ታዳጊዬ፣

የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤

ሕዝቤን የሚያስገዛልኝም144፥2 አንዳንዶች ሕዝቦችን የሚያሰገዛልኝ ይላሉ። እርሱ ነው።

3እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?

ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው?

4ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤

ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።

5እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያትህን ሰንጥቀህ ውረድ፤

ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስስ።

6የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤

ፍላጻህን ሰደህ ግራ አጋባቸው።

7እጅህን ከላይ ዘርጋ፤

ከኀይለኛ ውሃ፣

ከባዕዳንም እጅ፣

ታደገኝ፤ አድነኝም፤

8አንደበታቸው ሐሰትን ይናገራል፤

ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት።

9አምላክ ሆይ፤ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ፤

ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።

10ነገሥታትን ድል የሚያጐናጽፍ፣

ባሪያውን ዳዊትን ከሚጐዳ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።

11አንደበታቸው ሐሰትን ከሚናገር፣

ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው፣

ከባዕዳን እጅ፣

ታደገኝ፤ አድነኝም።

12ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣

የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣

ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ፣

እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ።

13ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣

የተሞሉ ይሁኑ፤

በጎቻችን እስከ ሺህ ይውለዱ፤

በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺህ ይባዙ።

14ከብቶቻችን ይክበዱ፤144፥14 ወይም መሪዎቻችን ይጠነክራሉ

አይጨንግፉ፤ አይጥፉም።

እኛም በምርኮ አንወሰድ፤

በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይሰማ።

15ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው፤

እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 144:1-15

第 144 篇

祈求拯救与丰裕

大卫的诗。

1耶和华——我的磐石当受称颂,

祂使我能争善战。

2祂是我慈爱的上帝,

我的堡垒,我的避难所,

我的拯救者,我的盾牌,

我投靠祂。

祂使列国臣服于我。

3耶和华啊,

人算什么,你竟顾念他?

世人算什么,你竟眷顾他?

4因为人不过像一口气,

他的年日不过像影子转眼消逝。

5耶和华啊,

求你打开天门,亲自降临;

求你触摸群山,使群山冒烟。

6求你发出闪电驱散敌人,

求你射出利箭击溃他们。

7求你从天上伸手从惊涛骇浪中拯救我,

从外族人手中拯救我。

8他们满口谎言,

起誓也心怀诡诈。

9上帝啊,我要向你唱新歌,

用十弦琴歌颂你。

10你使君王得胜,

救你的仆人大卫逃离刀剑的杀戮。

11求你从外族人手中拯救我,

他们满口谎言,

起誓也心怀诡诈。

12愿我们的儿子年轻时像茁壮的树木,

我们的女儿像宫殿中精雕的柱子。

13愿我们的仓库堆满各样的谷物,

我们的羊在田野繁衍众多,

成千上万。

14愿我们的牲口驮满货物144:14 牲口驮满货物”或译“繁殖众多”。

我们的城墙固若金汤,

无人被掳,街上没有哭叫声。

15生活在这种光景里的人有福了!

尊耶和华为上帝的人有福了!