መዝሙር 141 NASV - 诗篇 141 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 141:1-10

መዝሙር 141

የክፉዎችን ድሎት ላለመመኘት የቀረበ ጸሎት

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤

ወደ አንተ ስጣራም ድምፄን ስማ።

2ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ትቈጠርልኝ፤

እጄን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።

3እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤

የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።

4ከዐመፀኞች ጋር፣

በክፉ ሥራ እንዳልተባበር፣

ልቤን ወደ ክፉ አታዘንብል፤

ከድግሳቸውም አልቋደስ።

5ጻድቅ141፥5 ወይም ጻድቁ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤

ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስ ዘይት ነው፤

ራሴም ይህን እንቢ አይልም።

ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው፤

6ሹማምታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፣

ቃሌ የምታረካ ናትና፣ ይሰሟታል።

7ደግሞም፣ “ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣

እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል141፥7 አንዳንድ ትርጒሞች መቃብር ይላሉ። አፋፍ ላይ ተበታተነ” ይላሉ።

8ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ፤

መጠጊያዬም አንተ ነህ፤ እንግዲህ ነፍሴን አትተዋት።

9ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣

ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ።

10እኔ ብቻ በደኅና ሳመልጥ፣

ክፉዎቹ በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 141:1-10

第 141 篇

求上帝荫庇

大卫的诗。

1耶和华啊,

我向你呼求,求你快来帮助我;

我向你呼求的时候,求你垂听。

2愿我的祷告如香升到你面前,

愿我举手所献的祷告如同晚祭。

3耶和华啊,

求你守住我的口,

看住我的嘴。

4耶和华啊,求你不要让我的心偏向邪恶,

免得我与恶人同流合污;

也不要让我吃他们的美食。

5我情愿受义人出于爱心的责打,

他们的责打是良药,

我不会逃避。

我要不断地用祷告抵挡恶人的行径。

6他们的首领被抛下悬崖的时候,

他们就会知道我所言不虚。

7那些恶人的骨头散落在墓旁,

好像耕田翻起的土块。

8主耶和华啊,

我仰望你,我投靠你,

求你不要让我遭害。

9求你不要使我落入恶人设下的网罗,

不要掉进他们的陷阱。

10愿他们作茧自缚,

而我可以安然逃脱。