መዝሙር 14 NASV - 诗篇 14 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 14:1-7

መዝሙር 14

አምላክ የለሽ ሰዎች

14፥1-7 ተጓ ምብ – መዝ 53፥1-6

ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።

1ሞኝ14፥1 በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ሞኝ ወይም ተላላ ተብለው የተተረጐሙት የዕብራይስጥ ቃላት ግብረ ገባዊ ንቅዘትን የሚያመለክቱ ናቸው። በልቡ፣

“እግዚአብሔር የለም” ይላል።

ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤

በጎ ነገር የሚሠራ አንድም የለም።

2የሚያስተውል፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ መኖሩን ለማየት፣

እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።

3ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤

በአንድ ላይም ብልሹ ሆነዋል፤

አንድ እንኳ፣

መልካም የሚያደርግ የለም።

4የእግዚአብሔርን ስም የማይጠሩት፣

ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣

ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ዕውቀት የላቸውምን?

5ባሉበት ድንጋጤ ውጦአቸዋል፤

እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና።

6እናንተ የድኾችን ዕቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤

እግዚአብሔር ግን መጠጊያቸው ነው።

7ምነው እስራኤልን የሚያድን ከጽዮን በወጣ!

እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣

ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 14:1-7

第 14 篇

世人的邪恶

大卫的诗,交给乐长。

1愚昧人心里想:“没有上帝。”

他们全然败坏,行为邪恶,

无人行善。

2耶和华从天上俯视人间,

看有没有明智者,

有没有寻求上帝的人。

3人们都偏离正路,

一同堕落;

没有人行善,

一个也没有!

4恶人吞吃我的百姓如同吃饭,

他们不求告耶和华。

难道他们无知吗?

5但他们终必充满恐惧,

因为上帝站在义人当中。

6你们恶人使困苦人的计划落空,

但耶和华是他们的避难所。

7以色列的拯救来自锡安

耶和华救回祂被掳的子民时,

雅各要欢欣,以色列要快乐。