መዝሙር 139 NASV - 诗篇 139 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 139:1-24

መዝሙር 139

ሁሉን ዐዋቂ አምላክ

ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር ሆይ፤ መረመርኸኝ፤

ደግሞም ዐወቅኸኝ።

2አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤

የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ።

3መሄድ መተኛቴን አጥርተህ ታውቃለህ፤

መንገዶቼንም ሁሉ ተረድተሃቸዋል።

4እግዚአብሔር ሆይ፤ ገና ቃል ከአንደበቴ ሳይወጣ፣

እነሆ፤ አንተ ሁሉንም ታውቃለህ።

5አንተ ከኋላም ከፊትም ዙሪያዬን ከለልኸኝ፤

እጅህንም በላዬ አደረግህ።

6እንዲህ ያለው ዕውቀት ለኔ ድንቅ ነው፤

ልደርስበትም የማልችል ከፍ ያለ ነው።

7ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ?

ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?

8ወደ ሰማይ ብወጣ፣ አንተ በዚያ አለህ፤

መኝታዬንም በሲኦል139፥8 አንዳንድ ትርጒሞች በጥልቁ ውስጥ ይላሉ። ባደርግ በዚያ ትገኛለህ።

9በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበር፣

እስከ ባሕሩ ዳርቻ መጨረሻ ብሄድ፣

10በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች፤

ቀኝ እጅህም አጥብቃ ትይዘኛለች።

11እኔም፣ “ጨለማው በርግጥ ይሰውረኛል፤

በዙሪያዬ ያለውም ብርሃን ሌሊት ይሆናል” ብል፣

12ጨለማ የአንተን ዐይን አይዝም፤

ሌሊቱም እንደ ቀን ያበራል፤

ጨለማም ብርሃንም ለአንተ አንድ ናቸውና።

13አንተ ውስጣዊ ሰውነቴን ፈጥረሃልና፤

በእናቴም ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ።

14ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤

ሥራህ ድንቅ ነው፤

ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች።

15እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣

ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተደበቁም፤

በምድር ጥልቀት ውስጥ በጥበብ በተሠራሁ ጊዜ፣

16ዐይኖችህ ገና ያልተበጀውን አካሌን አዩ፤

ለእኔ የተወሰኑልኝም ዘመናት፣

ገና አንዳቸው ወደ መኖር ሳይመጡ፣

በመጽሐፍ ተመዘገቡ።

17አምላክ ሆይ፤ ለእኔ ያለህ ሐሳብ እንዴት ክቡር ነው!

ቍጥሩስ ምንኛ ብዙ ነው!

18ልቍጠራቸው ብል፣

ከአሸዋ ይልቅ ይበዙ ነበር።

ተኛሁም ነቃሁም፣

ገና ከአንተው ጋር ነኝ።

19አምላክ ሆይ፣ ክፉዎችን ብትገድላቸው ምናለበት!

ደም የተጠማችሁ ሰዎች ሆይ፤

ከእኔ ራቁ!

20ስለ አንተ በክፋት ይናገራሉና፤

ጠላቶችህም ስምህን በከንቱ ያነሣሉ።

21እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚጠሉህን አልጠላምን?

በአንተ ላይ የሚነሡትንስ አልጸየፍምን?

22በፍጹም ጥላቻ ጠልቻቸዋለሁ፤

ባላጋራዎቼም ሆነዋል።

23እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤

ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤

24የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ፤

በዘላለምም መንገድ ምራኝ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 139:1-24

第 139 篇

上帝的全知和佑护

大卫的诗,交给乐长。

1耶和华啊,你洞察我的内心,

知道我的一切。

2我或坐下或起来,你都知道,

你从远处就知道我的心思意念。

3我或外出或躺卧,你都了解,

你熟悉我的一切行为。

4耶和华啊,我话未出口,

你已洞悉一切。

5你在我前后护卫着我,

以大能的手保护我。

6这一切实在是太奇妙,

太深奥了,我无法明白。

7我去哪里可躲开你的灵?

我跑到哪里可避开你的面?

8我若升到天上,你在那里;

我若下到阴间,你也在那里。

9纵使我乘着晨风飞到遥远的海岸居住,

10就是在那里,

你的手必引导我,

你大能的手必扶持我。

11我想,黑暗一定可以遮蔽我,

让我四围变成黑夜。

12然而,即使黑暗也无法遮住你的视线。

在你看来,黑夜亮如白昼,

黑暗与光明无异。

13你创造了我,

使我在母腹中成形。

14我称谢你,

因为你创造我的作为是多么奇妙可畏,

我心深深知道。

15我在隐秘处被造、在母腹中成形的时候,

你对我的形体一清二楚。

16我的身体还未成形,

你早已看见了。

你为我一生所定的年日,

我还没有出生就已经记在你的册子上了。

17耶和华啊,

你的意念对我来说是何等宝贵,何等浩博!

18我若数算,它们比海沙还多。

我醒来的时候,

依然与你在一起。

19耶和华啊,愿你杀戮恶人!

嗜血成性的人啊,你们走开!

20他们恶言顶撞你,

你的仇敌亵渎你的名。

21耶和华啊,

我憎恨那些憎恨你的人,

我厌恶那些攻击你的人。

22我恨透了他们,

我视他们为敌人。

23上帝啊,求你鉴察我,

好知道我的内心;

求你试验我,好知道我的心思。

24求你看看我里面是否有邪恶,

引导我走永恒的道路。