መዝሙር 136 NASV - 诗篇 136 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 136:1-26

መዝሙር 136

ምስጋና በቅብብሎሽ መዝሙር

1እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

2የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

3የጌቶችን ጌታ አመሰግኑ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

4እርሱ ብቻውን ታላላቅ ታምራትን የሚያደርግ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

5ሰማያትን በብልኀት የሠራ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

6ምድርን በውሃ ላይ የዘረጋ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

7ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

8ፀሓይ በቀን እንዲሠለጥን ያደረገ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

9ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

10የግብፅን በኵር የመታ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

11እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

12በኀያል እጅና በተዘረጋች ክንድ ይህን ያደረገ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

13የኤርትራን ባሕር136፥13 ዕብራይስጡ ያመሱፍ የሚለው በቍ 15 ከሚገኘው ጭምር የሸምበቆ ባሕር ይለዋል። ለሁለት የከፈለ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

14እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

15ፈርዖንንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ያሰጠመ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

16ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

17ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

18ኀያላን ነገሥታትን የገደለ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

19የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን የገደለ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

20የባሳንን ንጉሥ ዐግን የገደለ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

21ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

22ለባሪያው ለእስራኤል ርስት አድርጎ የሰጠ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

23በውርደታችን ጊዜ ያሰበን፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

24ከጠላቶቻችን እጅ ያዳነን፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

25ለፍጡር ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

26የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 136:1-26

第 136 篇

上帝的慈爱永远长存

1你们要称谢耶和华,

因为祂是美善的,

祂的慈爱永远长存。

2你们要称谢万神之神,

因为祂的慈爱永远长存。

3你们要称谢万主之主,

因为祂的慈爱永远长存。

4要称谢那位独行奇事的,

因为祂的慈爱永远长存。

5要称谢那位用智慧创造诸天的,

因为祂的慈爱永远长存。

6要称谢那位在水上铺展大地的,

因为祂的慈爱永远长存。

7要称谢那位创造日月星辰的,

因为祂的慈爱永远长存。

8祂让太阳管理白昼,

因为祂的慈爱永远长存。

9祂让月亮星辰管理黑夜,

因为祂的慈爱永远长存。

10要称谢那位击杀埃及人长子的,

因为祂的慈爱永远长存。

11祂带领以色列人离开埃及

因为祂的慈爱永远长存。

12祂伸出臂膀施展大能,

因为祂的慈爱永远长存。

13要称谢那位分开海的,

因为祂的慈爱永远长存。

14祂引领以色列人走过海,

因为祂的慈爱永远长存。

15祂让法老和他的军兵葬身海,

因为祂的慈爱永远长存。

16要称谢那位带领其子民走过旷野的,

因为祂的慈爱永远长存。

17要称谢那位击杀强大君王的,

因为祂的慈爱永远长存。

18祂击杀了大能的君王,

因为祂的慈爱永远长存。

19祂击杀了亚摩利西宏

因为祂的慈爱永远长存。

20祂击杀了巴珊

因为祂的慈爱永远长存。

21祂把他们的土地赐给祂的子民作产业,

因为祂的慈爱永远长存。

22祂把他们的土地赐给祂的仆人以色列人作产业,

因为祂的慈爱永远长存。

23祂眷顾处于卑贱境地的我们,

因为祂的慈爱永远长存。

24祂拯救我们脱离仇敌,

因为祂的慈爱永远长存。

25祂赐食物给众生,

因为祂的慈爱永远长存。

26你们要称谢天上的上帝,

因为祂的慈爱永远长存。